ሊዮኔል ሜሲ በኢትዮጵያ ዐይነ-ስውራንን ለመደገፍ ከኦርካም ቴክኖሎጂ ጋር በትብብር ለመሥራት ተስማማ

ሊዮኔል ሜሲ በኢትዮጵያ ዐይነ-ስውራንን ለመደገፍ ከኦርካም ቴክኖሎጂ ጋር በትብብር ለመሥራት ተስማማ
አርጀንቲናዊው የእግር ኳስ ኮከብ ተጫዋች ሊዮኔል ሜሲ በኢትዮጵያ የሚገኙ ዐይነ-ስውራን ዜጎችን ለመደገፍ ከኦርካም ቴክኖሎጂ ጋር በትብብር ለመሥራት ተስማምቷል።
ተጫዋቹ በኢትዮጵያ የሚገኙ ዐይነ ስውራን ዜጎችን ለመደገፍ በመስማማቱም ክብር እንደሚሰማው በማኅበራዊ ትሥሥር ገጹ አስታውቋል።
የኦርካም ቴክኖሎጂ በሺህዎች የሚቆጠሩ ዐይነ ስውራንን ሕይወት እያሻሻለ ያለው ሊዮኔል ሜሲ፣ ቴክኖሎጂው ዐይነ ስውራን ሕልሞቻቸውን እንዲያሳኩ ይረዳቸዋል ብሏል።
የቀዳማዊ እመቤት ጽ/ቤት በቅርቡ የዘመኑ የቴክኖሎጂ ውጤት የሆነ “OrCam MyEye” የተሰኘ ዐይነ ስውራንን የሚያግዝ መነፅር ለሁለት ሺህ ዐይነ ስውራን አስረክቧል።
መሣሪያው አማርኛም ሆነ እንግሊዝኛ የሚያነብብ ሲሆን የገንዘብ ኖቶችን ለይቶ ለተጠቃሚው ያስረዳል፤ የቀለም ዓይነትን ይለያል እንዲሁም ከፊት ለፊት ምን እንዳለ እና ማን እንደመጣ መዝግቦ በመያዝ መረጃ ይሰጣል።

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትስስር ይፍጠሩ

325,851FansLike
49,039FollowersFollow
13,194SubscribersSubscribe