ላሊበላ ከተማ ወደ ነበረችበት ለመመለስ ብዙ ዓመታት ያስፈልጓታል ተባለ

የህወሓት ታጣቂዎች በላሊበላ ከተማ መጠነ ሰፊ የኢኮኖሚ ውድመት በማደርሳቸው ወደ ነበረችበት ለመመለስ በርካታ ዓመታት ያስፈልጋታል ተባለ፤

በከተማዋ የመንግስትና የግለሰቦች ንብረት ወድሟል፤ የመብራትና የውኃ ችግር ለከተማዋ ፈተና መሆኑም ተሰምቶአል።

የቅዱስ ላሊበላ ከተማ አስተዳደር ባህል ቱሪዝምና ስፖርት መምሪያ ኃላፊ አቶ መልካሙ ዓለሙ እንደተናገሩት የህወሓት ኃይሎች የዓለም የትምህርት፣ የሳይንስና የባህል ድርጅት (UNESCO) በዓለም ቅርስነት የመዘገባቸዉ የቅዱስ ላሊበላ አቢያተ ክርቲያናት ላይ በቀጥታም ባይሆን በተዘዋዋሪ መንገድ ጉዳት አድርሰዋል፣ በካህናቱም ላይ ችግር እንዲደርስባቸው አድርገዋል፡፡

መሰረተ ልማትን በተመለከተ በላሊበላ አጠቃላይ ውድመት መድረሱም የጠቀሱት ሃላፊው ቡድኑ ሰነዶችን ሁሉ በእሳት አቃጥሎአል፤የላሊበላ አውሮፕላን ማረፊያ አገልግሎት እንዳይሰጥ ሆኖ መዉደሙም ተናግረዋል።

ከተማዋን ወደነበረችበት ለመመለሰ ወራትን ምናልባትም ዓመታትን ሊወስድ እንደሚችል ነዉ የተነገረዉ። በከተማዋ የመብራት፣ የውኃና የሆቴል አገልግሎቶች በሙሉ ከጥቅም ውጭ መሆናቸውም ታዉቋዋል፡፡ በጦርነቱ ምክንያት ወደ ሌሎች አካባቢዎች ተፈናቅለው የነበሩ ነዋሪዎች አሁን ወደ ቀያቸው እየተመለሱ እንደሆ ተዘግቦአል።

ያም ሆኖ ከተማዋ መጪውን የገና በዓል በድምቀት ለማክበር ከወዲሁ እንቅስቃሴ እያደረገች ነው፡፡

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትስስር ይፍጠሩ

325,851FansLike
49,039FollowersFollow
13,194SubscribersSubscribe