ሌ/ጀነራል ጻድቃን ገብረ ትንሳዔን ጨምሮ 40 የቀድሞ የኢትዮጵያ አየር ሃይልና የፖሊስ አመራሮች ላይ የመያዣ ትእዛዝ ወጣ

ሌ/ጀነራል ጻድቃን ገብረትንሳዔን ጨምሮ 40 የቀድሞ የኢትዮጵያ አየር ሃይል፣ የሀገር መከላከያና የፖሊስ አመራሮች ላይ የመያዣ ትእዛዝ ወጣ።
በሀገር ክህደት እና የሀገር መከላከያና የፌደራል ፖሊስ አባላትን በማሳገት የተጠረጠሩ ከፍተኛ የቀድሞ የኢትዮጵያ አየር ሃይል፣ የሀገር መከላከያና የፖሊስ አመራሮች ላይ የመያዣ ትዕዛዝ ወጣ
በሀገር ክህደት እና የሀገር መከላከያና የፌዴራል ፖሊስ አባላትን በማሳገት የተጠረጠሩ ከፍተኛ የቀድሞ የኢትዮጵያ አየር ሃይል፣ የሀገር መከላከያና የፖሊስ አመራሮች ላይ የመያዣ ትዕዛዝ መውጣቱን የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን አስታወቀ፡፡
ከመንግስት እና ህዝብ የተጣለባቸውን ከባድ ኃላፊነት ወደ ጐን በመተው መቀመጫቸውን ትግራይ ክልል ካደረጉ ፀረ-ሠላም እና ፀረ-ህዝብ የህዋሃት ከፍተኛ አመራሮች ተልዕኮ በመቀበልና በጽንፈኝነት አስተሳሰብ በመነሣት እንዲሁም ህገ-መንግስታዊ ሥርአቱን አደጋ ላይ የሚጥል ተግባር ውስጥ በቀጥታ እና በተዘዋዋሪ መንገድ በመሳተፍ በአገር ክህደት እና በሰብአዊ መብት ጥሰት ወንጀል ቀደም ሲል የመያዣ ትዕዛዝ ከወጣባቸው በተለያየ የሃላፊነት እርከን ላይ ከሚገኙ ወታደራዊ አመራሮች በተጨማሪ በሀገር ላይ ጥቃት ለመፈፀም በማቀድ በግንባር የተሰማሩና ጥቅምት 24 ቀን 2013 ዓ.ም በሀገር መከላከያ ሰራዊትና በፌዴራል ፖሊስ አባላት ላይ የተካሄደውን አሳፋሪ የእገታ ተግባር እንደመሩና እንዳስተባበሩ በምርመራ የተደረሰባቸው አርባ የከዱና በጡረታ የተገለሉ የኢትዮጵያ አየር ሃይል፣ የሀገር መከላከያና የፌዴራል ፖሊስ ተጠርጣሪ አመራሮች ላይ የመያዣ ትዕዛዝ ወጥቶባቸዋል።
በዚህም መሰረት፡-
ሜጀር ጀነራል ፃድቃን ገ/ትንሳኤ ፣ኮሎኔል በርሄ ወልደ ሚካኤል ገብሩ ፣
ኮሚሽነር ይህደጎ ስዩም ወልደማርያም ጨምሮ የኢትዮጵያ አየር ሃይል፣ የሀገር መከላከያና የፌዴራል ፖሊስ ተጠርጣሪ አመራሮች ላይ የመያዣ ትዕዛዝ ወጥቶባቸዋል።
በመሆኑም መላው የሃገራችን ህዝብ በተለይም ደግሞ ሰላም ወዳዱ የትግራይ ህዝብ፣ የሀገር መከላከያ ሰራዊት፤ የአገራችን የፖሊስ ሰራዊትና የደህንነት ተቋማት እነዚህን የጁንታው ህዋሃት ጥፋት ቡድን አባላት አድኖ ለህግ ለማቅረብ እየተደረገ ባለው ጥረት በያላችሁበት የድርሻችሁን እንድትወጡ ኮሚሽኑ ጥሪ እያቀረበ በቀጣይ መቀሌ ከተማ የገባው የኮማንዶና የወንጀል ምርመራ ቡድን በሚያደርገው አሰሳና ኦፕሬሽን የሚገኙ ውጤቶችን እየተከታተለ በመገናኛ ብዙሃን በኩል ለህብረተሰቡ ይፋ የሚያደርግ መሆኑን አስታውቋል፡፡

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትስስር ይፍጠሩ

325,851FansLike
49,039FollowersFollow
13,194SubscribersSubscribe