ሕወሃት ጦር መሳሪያዎቹንና ወታደራዊ ቁሳቁሶቹን ለኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት የማስረከቡ ተስማ

– የአፍሪካ ኅብረት ተቆጣጣሪ ቡድን የሕወሃትን ጦር መሳሪያዎች ለኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት የማስረከቡን ሂደት አስፈጽሜያለሁ ማለቱ ተገለጠ።

አፍሪካ ኅብረት በኢትዮጵያ መንግሥትና ሕወሃት መካከል የተፈረመውን የግጭት ማቆም ስምምነት አተገባበር እንዲከታተልና እንዲቆጣጠር ያቋቋመው ተቆጣጣሪ ኮሚሽን ማምሻውን መቀሌ ላይ ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥቷል።

የኅብረቱ ተቆጣጣሪ ኮሚሽን፣ ሕወሃት ጦር መሳሪያዎቹንና ወታደራዊ ቁሳቁሶቹን ለኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት የማስረከቡን ሂደት አስፈጽመናል ማለቱን የትግራይ ክልል ቴሌቩዥን ዘግቧል። የመከላከያ ሠራዊትና የሕወሃት ወታደራዊ ተወካዮችም፣ ትጥቅ የማስፈታት፣ የመበተንና ትጥቅ የፈቱ ታጣቂዎችን መልሶ የማዋሃዱን እንዲሁም ሌሎች የታጠቁ ኃይሎችን ከትግራይ የማስወጣቱን ሂደት ተግባራዊ ማድረግ ጀምረናል ማለታቸውን ዘገባው ጠቅሷል።

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትስስር ይፍጠሩ

325,851FansLike
49,039FollowersFollow
13,194SubscribersSubscribe