መላው የኢትዮጵያ ህዝቦች ከመከላከያ ሰራዊት ጐን በመሆን ለአገራችን ዘብ እንድንቆም ጥሪያችንን እናስተላልፋለን ሲል የህዝብ ተወካዮች ም/ቤት ጥሪ አቀረበ።
የህዝብ ተወካዮች ም/ቤት ዛሬ ባወጣው መግለጫ የአገራችንን ሉአላዊነት ከማስከበር አልፎ ህዝባችን ድጋፍ በፈለጉበት መስክ ሁሉ በመሰማራት የቁርጥ ቀን ልጅ የሆነውን የመከላከያ ሰራዊታችንን መተናኮስ የኢትዮጵያ ህዝቦች ሊታገሱት የማይችሉት እኩይ ተግባር ነው ብሏል፡፡
ምክር ቤቱ መላው የኢትዮጵያ ህዝቦች ከጀግናው የመከላከያ ሰራዊታችን ጐን በመቆም የአገራችንን ሉአላዊነትና አንድነት የምናስጠብቅበት ወሳኝ ምዕራፍ ላይ እንገኛለን ሲል በማህበራዊ ገፁ አስታውቋል፡፡

