መንታ ልጆችን እንዴት ማርገዝ ይቻላል?

ለወትሮው ቢሆን መንታ መውለድ ለብዙዎች አስገራሚና አስደሳች ክስተት መሆኑ አጠያያቂ አይደለም።
በተለይ የልጆቻቸው ቁጥር ከሁለት እንዲበልጥ ለማይፈልጉና በእርግዝና ወቅት ተያይዘው የሚመጡ ጫናዎችን ዳግም ማየት ለማይልጉ ወላጆች መንታ መውለድ ከደስታው ባሻገር እረፍትና እፎይታን ነው።
ደቡብ አፍሪካዊ ናት። ፕሪቶሪያ ውስጥ ነው የምትኖረው። ጎሳሜ ታማራ ትባላለች። ከዚህ በፊት 2 ልጆች የነበሯት የ37 ዓመቷ ይህቺ እንስት አሁን ደግሞ 7 ወንዶችንና 3 ሴቶችን በአንድ ጊዜ ወልዳለች።
5ቱን በተፈጥሮአዊ መንገድ ስትውልድ 5ቱን ደግሞ በቀዶጥገና ነው የወለደችው ይላል የቢቢስ ዘገባ፡፡
አሁን አሁን በአለማችን ላይ ብዙ ልጆችን የሚወልዱ እናቶች እዚህም እዛም ይታያሉ።
ለምሳሌ እ.አ.አ በ2009 አንዲት አሜሪካዊት እናት 8 ልጆችን በአንድ ጊዜ በመውለድ የአለማችን የድንቃድንቅ መዝገብ ላይ መስፈር ችላ የነበረ ሲሆን፤ ባሳለፍነው ወር ደግሞ ከወደ ማሊ አንዲት የ25 ዓመት እናት 9 ልጆችን በመውለድ ሪከርዱን በእጇ አስገብታ ነበር።
የቢቢሲዋ ዘጋቢ ሮዳ ኦዲያምቦ እንደምትለው ከሆነ በርከት ያሉ ልጆችን በአንድ ጊዜ መውለድ እምብዛም የተለመደ አይደለም።
እንዲህ ያሉ ልጆችን ለመውለድ የተለያዩ የህክምና ድጋፎችን መጠቀም ያሻል ብትልም 10 (አስር) ልጆችን በአንዴ የወለዱት ጥንዶች ግን እርግዝናቸው ተፈጥሮአዊ እንደሆነ ያስረዳሉ።
በርግጥ መንታ የማርገዝ እድልን እንዴት ማስፋት ይቻላል?
ዶክተሮች በአንዳንድ አርግዝናዎች ላይ እንዴት መንትዮችን ማርገዝ እንደሚቻል ሙሉለሙሉ አልተረዱትም ይላሉ የዘረፉ ባለሙያዎች።
ብዙ ጊዜ በማህፀን ውስጥ ሁለት የዳበሩ እንቁላሎችን የወንድ የዘር ፍሬ ሲያገኛቸው አልያም፤ አንድ እንቁላል ከወንድ ዘር ጋር ከተገናኘ በኋላ ለሁለት ከተከፈለ መንትያዎች የመፈጠር እድል አላቸው የሚል እንዲሁ አጠቃላይ መላምት ቢኖራቸውም፤ እስካሁን በደረሱበት ምርምር ግን መንታ ልጆች ሊረገዙባቸው የሚችሉባቸውን ምክንያቶችን ያስቀምጣሉ:-
 እድሜ
እንደ የሴቶች ጤና ቢሮ መረጃ ከሆነ እድሜዋ 30 አልያም ከሰላሳ በላይ የሆነች ሴት መንታ የመፀነስ እድሏ የሰፋ ነው።
ለዚህ ዋነኛው ምክንያት በዚህ እድሜ ላይ የሚገኙ ሴቶች በመራቢያ ወቅታቸው ጊዜ በርከት ያሉ እንቁላሎችን ያመርታሉ።
ታዲያ በዚህ ጊዜ የወንድ የዘር ፍሬ ሁለት እንቁላሎችን የመስበር አቅም ካለው መንትዮች ይፈጠራሉ።
 በቤተሰብ ውስጥ መንታ የመውለድ ታሪክ
ከአባታቸው ይልቅ በእናታቸው በኩል መንታ የመውለድ ታሪክ ያላቸው ሴቶች መንትዮችን የመውለድ እድላቸው በጥቂቱም ቢሆን፤ እንደዚህ አይነት ታሪክ በቤተሰባቸው ውስጥ ከሌላቸው ሴቶች የተሻለ መንታዎችን የማርገዝ እድል አላቸው።
በተለይ የማይመሳሰል መንትያ ያላቸው ሴቶች ከ1 እስከ 60 በሚሆኑ የእርግዝና ጊዜአቸው መካከል መንትዮችን የመፀነስ እድል አላቸው።
ነገር ግን የማይመሳሰል መንትያ ያላቸው ወንዶች መንታ ልጆችን ማስፀነስ የሚችሉበት እድላቸው ከ1 እስከ 125 በሚደርሱ እርግዝናዎች ውስጥ ነው።
በነራችን ላይ አንዳንዶች መንታ ልጆችን መውለድ ከትውልድ ትውልድ የሚሸጋገር ክስተት ነው ሲሉ ቢደመጡም ይህን ጉዳይ የሚደግፉ ማስረጃዎች እምባዝም አይገኙም።
 የሕክምና ድጋፍ
እንደባለሙያዎቹ ገለፃ ከሆነ የመራባት ሕክምናን በመውሰድ መንታ ልጆችን ማርገዝ የሚቻልባቸው የተለያዩ መንገዶች አሉ።
ለዚህ ጉዳይ ከሚውሉ መድሃኒቶች መካከል አንዳዶቹ ስራቸው የሴቶችን እንቁላል ማነቃቃት ሲሆን ይህም ሴቶቹ በርካታ እንቅላሎችን በአንድ ጊዜ ማምረት እንዲችሉ ያደርጓቸዋል።
ይሄን ጊዜ የወንዱ ዘር ሁለት እንቁላሎችን የመስበር አቅም ካገኘ መንታ ልጆች ይፀነሳሉ። በብልቃጥ ውስጥ የሚደረገውም እንቁላልን የማዳበር ስራ መንታዎች እንዲፈጠሩ የማድረግ አቅም አለው።
በዚህ ጊዜ ባለሙያዎቹ የሴቶችን እንቁላል በመውሰድ በላብራቶሪ ውስጥ ከወንድ ዘር ጋር በማዳቀል ሽል ይፈጥሩና መልሰው ወደሴቷ ማህፀን ያስገቡታል፡፡ በዚህም መንታዎችን ማግኘት እንደሚቻል ያስረዳሉ።
ታዲያ በዚህ መንገድ መንታዎች የማግኘት እድልን ለማስፋት ባለሙያዎቹ ሁለት ሽሎችን ወደ ማህፀን ያስገባሉ፡፡
ነገር ግን የበሽታ መቆጣጠሪያ እና መከላከያ ማዕከል (CDC) ይህን መንገድ ለመጀመሪያ ጊዜ የሚጠቀሙ ወጣት ሴቶች ወደ ማህፀናቸው አንድ ሽል ብቻ እንዲያስገቡ አበክሮ መምከሩም ሳይዘነጋ፡፡
 ቁመትና ክብደት
ቁመታቸው ረዘም ያሉና ክብደታቸውም ከፍ ያሉ ሴቶች ቢያንስ የማይመሳሰሉ መንትዮችን የማርገዝ እድላቸው ሰፋ ያለ ነው ይላሉ የዘርፉ ባለሙያዎች።
በርግጥ ለዚህ ምክንያት ግልፅ የሆነ ማስረጃ የሌለ ቢሆንም እንደመላምት ግን እነዚህ ሴቶች በአመጋገብ ስርዓታቸው የተሻሉ ሊሆኑ ስለሚችሉና ሰውነታቸውም ገዘፍ ያለ በመሆኑ ሁለት ፅንሶችን ለመፍጠር የሚያስችል ግብዓት ሰውነታቸው ሳያዘጋጅ አይቀርም ይላሉ።
መልካም ጤንነት!!

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትስስር ይፍጠሩ

325,851FansLike
49,039FollowersFollow
13,194SubscribersSubscribe