መንግስት ለ2015 በጀት አመት ለመከላከያ ሠራዊት 100 ቢሊዮን እንደተመደበለት ተሰማ

ገንዘብ ሚንስቴር ለ2015 ዓ፣ም 785 ቢሊዮን ብር አጠቃላይ ረቂቅ በጀት አዘጋጅቶ ለሚንስትሮች ምክር ቤት እንደላከ ሪፖርተር ዘግቧል።
 ከዚህ ረቂቅ በጀት ውስጥ ለመከላከያ ሠራዊት 100 ቢሊዮን እንደተመደበለት ዘገባው ከምንጮች መስማቱን ጠቅሷል።
 በዘንድሮው በጀት ዓመት ለመከላከያ ሠራዊት የተመደበው 22 ቢሊዮን ብር ነበር። መንግሥት ባዘጋጀው አዲስ ረቂቅ በጀት ከባለ በጀት መስሪያ ቤቶች ላይ እስከ 40 በመቶ የሚደርስ በጀት ተቀንሶባቸዋል።
ከውጭ ምንጮች ይገኛል ተብሎ የሚጠበቀው 64 ቢሊዮን ብር እስካሁን ያልተሟላ ሲሆን፣ መንግሥት የበጀት ጉድለቱን ከአገር ውስጥ ምንጮች ለማሟላት አስቧል።

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትስስር ይፍጠሩ

325,851FansLike
49,039FollowersFollow
13,194SubscribersSubscribe