መንግስት የስራ መኪና ከቀረጥ ነፃ እንዲገባ የሚፈቅድ መመሪያ አወጣ

የገንዘብ ሚኒስቴር በማምረቻ ኢንዱስትሪ፣ በግብርና ፣ በሎጀስቲክስ፣ በኮንስትራክሽን፣ የባለኮከብ ሆቴሎች ኢንቨስትምንትን ጨምሮ ለልማት ፕሮጀክቶች የሚውሉ ተሽከርካሪዎች ከቀረጥ ነፃ እንዲገቡ መፍቀዱን ሪፖርተር ጋዜጣ አስነብቧል።

በገንዘብ ሚኒስቴር የተዘጋጀው አዲስ መመሪያ ” ለልማት ፕሮጀክቶች ከቀረጥ ነፃ ወደ አገር የሚገቡ ተሽከርካሪዎችን ለመወሰን የወጣ መመሪያ ” የሚል ስያሜ የተሰጠው ነው ተብሏል።

ይህም የደረቅ፣ የፍሳሽ ወይም ማቀዝቀዣ የተገጠመለት የጭነት መኪናን ወይም ለተለየ አገልግሎት ተብለው የሚዘጋጁ አውቶብስን፣ ሚኒባስን፣ ሚዲባስን፣ ሽፍን የዕቃ ማጓጓዣ ተሽከርካሪንና የሞተር ብስክሌቶችን ይጨምራል፡፡

መመሪያው የማበረታቻው ተጠቃሚ የኢንቨስትመንት መስኮች ብሎ ከለያቸው ውስጥ ፦

– በማምረቻ ኢንዱስትሪ፣
– የኢንዱስትሪ ፓርክ ልማት፣
– በግብርና
– በሎጀስቲክስ
– በኮንስትራክሽን ሥራ ተቋራጭነት፣
– ባለ ኮከብ ሆቴሎች (የሪዞርት ሆቴሎችን ጨምሮ)
– በባቡር መሠረተ ልማት
– ሞቴሎች
– ሬስቶራንቶችና ሎጆች የተሰማሩ ባላሀብቶች ይገኙበታል፡፡

በተጨማሪም ፦

– በመረጃና መገናኛ ቴክኖሎጂ ልማት፣
– በአስጎብኝ ሥራ
– በኤክትሪክ ኃይል ማመንጫ፣ ማስተላለፊያና ማሠራጫ፣
– በትምህርትና ሥልጠና፣
– የጤና አገልግሎት የኢንቨስትመንት መስኮች የተሰማሩ ባለሀብቶች ተሽርካሪዎችን ከቀረጥ ነፃ እንዲያስገቡ ይፈቅዳል።

የአርክቴክቸርና ኢንጂነሪንግ ሥራዎች የቴክኒክ ምርመራና ትንተና አገልግሎትና ንግድ የሥራ መስኮች አዳዲስ ፕሮጀክቶችን የሚያቋቋሙ ወይም ነባር ደርጅታቸውን የሚያስፋፉ ባለሀብቶችም የዕድሉ ተጠቃሚ እንደሚሆኑ ታውቋል፡፡

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትስስር ይፍጠሩ

325,851FansLike
49,039FollowersFollow
13,194SubscribersSubscribe