መንግስት የ 5 አመት የመንግስት ቦንድ ማተሙን የገንዘብ ሚኒስትር አስታወቀ

መንግስት በበጀት አመት መካከል ለሚያጋጥመዉ የገንዘብ እጥረት ከብሔራዊ ባንክ የሚወስደውን የቀጥታ ብድር በሚተካ መልኩ የ 5 አመት የመንግስት ቦንድ ማተሙን የገንዘብ ሚኒስትሩ አህመድ ሽዴ ተናግረዋል ሲል ብስራት ራዲዮ አስደምጧል።

በቦንዱም 25.6 ቢሊዮን ብር የበጀት መሸፈኛ ማግኘት መቻሉን ሚኒስትሩ ገልጸዋል። አዲስ በተጀመረዉ በዚህ መላ መንግስት የረጅም ግዜ ብድር ከሀገር ዉስጥ ገበያ እንዲያገኝ እንደሚያስችለዉ ተናግረዋል።

ከዚህ ቀደም ከብሔራዊ ባንክ በቀጥተኛ ብድር የሚወሰደዉን ገንዘብ የሚያስቀርና የብድር ጫናን ለመቀነስ የሚያግዝ መሆኑን አክለዋል። በተመሳሳይ ዘንድሮ ለብሔራዊ ባንክ መከፈል የነበረበትን የብድር ገንዘብ ወደ ረጅም ግዜ የብድር ዋስትና በመቀየር በጀት ላይ የሚኖረዉን ጫና በመጠኑ መቀነስ መቻሉን ጠቁመዋል።

በሌላ በኩል ሊከሰት የሚችለዉን የበጀት እጥረት ለመቀነስ እንዲረዳ በሚል በ 2015 አመት በጀት ተይዞላቸዉ ያልተጀመሩ ፕሮጀክቶችን ወደ ሚቀጥለዉ አመት በማሸጋሸግ 18.2 ቢሊዮን ብር ወጪ ለመቀነስ እንደተቻለም አንስተዋል።

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትስስር ይፍጠሩ

325,851FansLike
49,039FollowersFollow
13,194SubscribersSubscribe