መንግስት ዲፕሎማቶች ወደ መቀሌ እንዲሄዱ ፈቀደ

ሕወሃት ከፌደራል መንግሥት ጋር ለሚያደርገው ድርድር ቅድመ ሁኔታ አስቀመጠ፤

ሕወሃት ከፌደራል መንግሥት ጋር ለሚያደርገው ድርድር ቅድመ ሁኔታና የጊዜ ገደብ ማስቀመጡን የሕወሃት ሊቀመንበር ዶ/ር ደብረጺዮን ገ/ሚካዔል ተናገሩ፡፡

ዶ/ር ደብረጺዮን ለቪኦኤ እንደተናገሩት ከሰላም ድርድር በፊት መንግሥት ለትግራይ ያቋረጣቸውን መሠረታዊ አገልግሎቶች እንደገና መጀመር እንዳለበት አውስተዋል።

ዶ/ር ደብረጺዮን መንግሥት መሠረታዊ አገልግሎቶችን የሚቀጥልበትን ቁርጥ ያለ ቀን አሜሪካኖች ጠይቀው እንዲነግሯቸው የጊዜ ገደብ መስጠታቸውንም ቪኦኤ ዘግቧል፡፡

መሠረታዊ አገልግሎቶቹ የማይጀመሩ ከሆነ ግን ውጊያ እንከፍታለን ሲሉ ማስጠንቀቃቸዉንም ነዉ ዘገባዉ ያመለከተዉ፡፡

ፌደራል ምንገስት በበኩሉ ከህወሃት ጋር ያለምንም ቅድመ ሁኔታ ለመደራደር ያሰወቀ ሲሆን ተቀማጭነታቸው አዲስ አበባ የሆኑ ዲፕሎማቶች ወደ መቀሌ ሄደው ሁኔታውን እንዲመለከቱ ከወራት በፊት ለጠየቁት ጥያቄ መንግስት ሰሞኑን ፈቃድ መስጠቱን አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን አስታውቀዋል፤

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትስስር ይፍጠሩ

325,851FansLike
49,039FollowersFollow
13,194SubscribersSubscribe