መኢአድ አርበኞች ግንቦት ሰባትን አስጠነቀቀ

‹‹እንኳን ከመኢአድ ከሌሎቹም ጋር አልተዋሀድንም››

አርበኞች ግንቦት ሰባት

አርበኞች ግንቦት ሰባት ከመላው ኢትዮጵያውያን አንድነት ድርጅት (መኢአድ) ጋር ምንም ዓይነት ውህደት ሳይኖረው፣ የተዋሀደ አስመስሎ በተለያዩ መገናኛ ብዙኃን የሚያስነግረውን ዜና በአስቸኳይ እንዲያቆም አስጠነቀቀ፡፡

አርበኞች ግንቦት ሰባት በበኩሉ ስለውህደት መወያየቱን እንጂ፣ እንኳን ከመኢአድ ጋር ከሌሎቹም ፓርቲዎች ጋር አለመዋሀዱን አስታውቋል፡፡

የመኢአድ ዋና ጸሐፊ አቶ ካሳሁን አበባው እንደገለጹት፣ አርበኞች ግንቦት ሰባት ከመኢአድ ጋር እንደተዋሀደ አስመስሎ የሚናገረው ከእውነት የራቀ ነው፡፡ የመኢአድ ደጋፊዎችም ሆኑ አባላት ምንም የሚያውቁት ነገር ስለሌለ በአስቸኳይ ከድርጊቱ እንዲቆጠብ አሳስበዋል፡፡

አርበኞች ግንቦት ሰባት የመኢአድን ደጋፊዎችና አባላትን ለመከፋፈል፣ አገርንና ሕዝብን ወደ ተሻለ ደረጃ ለማሸጋገር የተያዘውን መልካም ጅማሮ ለማደናቀፍ ሆን ብሎ ያደረገው አደገኛ አካሄድ በመሆኑ፣ መኢአድ እንደሚያወግዘው ዋና ጸሐፊው ገልጸዋል፡፡

አርበኞች ግንቦት የጀመረውን የመከፋፈል ፖለቲካዊ ሴራ እንዲያቆምና በግልጽ ወጥቶ ይቅርታ እንዲጠይቅም አሳስበዋል፡፡

አርበኞች ግንቦት ሰባት እንኳን ከመኢአድ ጋር ከሌሎች ፓርቲዎችም ጋር እንዳልተዋሀደ፣ በመገናኛ ብዙኃንም የሰጠው መግለጫ ስለመዋሀድ ሳይሆን ‹‹እንዴት እንዋሀድ?›› በማለት የተደረገ ውይይት መሆኑን፣ የፖለቲካ ዘርፍ ኃላፊው አቶ ኤፍሬም ማዴቦ ማስተባበያ ሰጥተዋል፡፡

‹‹ተዋሀድን የሚል መግለጫ ሰጥተን አናውቅም፤›› ያሉት አቶ ኤፍሬም፣ አምስቱ ድርጅቶች አርበኞች ግንቦት ሰባት፣ ሰማያዊ ፓርቲ፣ መኢአድ፣ ኢዴፓና መኢዴፓ አንድ ላይ ሆነው አመራራቸውን ከመረጡ በኋላ ስለሚከስሙ፣ የዚያን ጊዜ ውህደት እንደሚፈጠር ከሚያውቁ በስተቀር ከመኢአድ ጋር ውህደት ፈጽመናል አለመባሉን አስረድተዋል፡፡

Kumneger Media
Kumneger Media
Kumneger Media is a News and Entertainment Website & Channel. Kumneger Media in addition to News and Entertainment it is the hub of Politics, Movies, Drama, Music, Comedy, Documentary and More!

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትስስር ይፍጠሩ

325,851FansLike
49,039FollowersFollow
13,194SubscribersSubscribe