መከላከያ ለሁለት ተከፍሎ እንደነበር ጀነራል አበባው ታደሰ ተናገሩ፤

በጦርነቱ ዋዜማ  በከዱ የሠራዊት አባላትና መኮንኖች ምክንያት  መከላከያ ለሁለት ተከፍሎ እንደነበር ጀነራል አበባው ታደሰ ተናገሩ፤

ጦርነቱ የተካሄደው 44 ሺ ለ250 ሺ ሰራዊት ነበር ተብሏል፤

አሸባሪው ህወሃት ጥቅምት 24 ሌሊት የሰሜን ዕዝን በተኛበት አሰቃቂ ጭፍጨፋ ከማድረጉ ቀደም ብሎ በሠራዊቱ ውስጥ ያሉትን ትግርኛ ተናጋሪ መኮንኖችን አስቀድሞ እንዲከዱ ማደረጉን የጦር ሀይሎች ምክትል ኢታማዢር ሹም ጀነራል አበባው ታደሰ ተናገሩ፤

ጀነራል አበባው ከኢቲቪ ጋር ባደረጉት ቆይታ ህወሃት ጦርነቱን ከመጀመሩ በፊት ከፍተኛ ወታደራዊ ዝግጅት ያደርግ እንደነበር ጠቅሰው በሰሜን ዕዝ ላይ አሰቃቂ ጭፍጨፋ ሲወስድ የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት ጥቃቱን በመከላከልና በማጥቃት ወደ መቀሌ የገባው ባለው አነስተኛ ወታደር ነው ብለዋል፤

ጦርነቱን ህወሃት ሲጀምረው የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት ቁጥር አነስተኛ  እንደነበር የጠቀሱት ጀነራሉ እነርሱ ግን አስቀድመው ባሰባሰቡት ወራሪ ሀይልና ከመከላከያ ከድተው የሄዱ አመራሮችን በመያዛቸው ጦርነቱ የተካሄደው 44 ሺ ለ250 ሺ ወታደር ነበር ብለዋል፡፡ ስሌቱ 12 ክፍለ ጦር  ለ 56 ክፍለ ጦር እንደነበር በመግለፅ፤

ያም ሆኖ ሶስት ሳምንት ባልሞላ ጊዜ ውስጥ መቀሌን ለመቆጣጠር ተችሏል ያሉት ጀነራሉ ይህም መከላከያ ድሉን ያገኘው ከግማሽ በላይ የሆነው የሠራዊቱ አባላት ከድተው ሠራዊቱ ለሁለት በተከፈለበት ወቅት መሆኑ የሰራዊቱ ግብ ሰንደቅ አላማውን ማስከበርና ሀገርን ከመፍረስ መታደግ  መሆኑን ያሳያል ብለዋል፤

ህወሃት በስልጣን ላይ በነበረበት ጊዜ  በሠራዊቱ ላይ ከፍተኛ ደባ ይፈፅም እንደነበር የሚገልፁት ጀነራሉ  በአማካይ ከ15 ሺ እስከ 20 ሺ ወታደር ይከዳ እንደነበርና ከሶስት ዓመት በፊት ለውጡን ተከትሎ መከላከያን በአዲስ መልክ ለማደራጀት ሲሰራ ፊፎርሙ እንዳይሳካ  መሰናክል ይፈጥር እንደነበር ተናግረዋል፤

በሌላ በኩል ህወሃት ጦር ነቱን ከመቀስቀሱ በፊት በመከላከያ ውስጥ የተሰራው ሪፎርም የተሳካ እንደነበር በወቅቱ መከላከያ ሚኒስቴር ከፍተኛ መኮንኖች  ይፋ ማድረጉ  ይታወሳል፤

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትስስር ይፍጠሩ

325,851FansLike
49,039FollowersFollow
13,194SubscribersSubscribe