ሚኒስትር ፊልሰን አብዱላሒ የሥልጣን መልቀቂያ ደብዳቤ ማስገባታቸውን አስታወቁ

የኢትዮጵያ የሴቶች ሕፃናትና ወጣቶች ሚኒስትር ፊልሰን አብዱላሒ የሥልጣን መልቀቂያ ደብዳቤ ማስገባታቸውን አስታወቁ።

ሚኒስትሯ የሥልጣን መልቀቂያ ደብዳቤ ያስገቡት ሰኔ 14 ቀን 2013 ዓ.ም. ከተካሔደው ምርጫ በኋላ አዲስ የፌድራል መንግሥት ሊመሰረት አንድ ሳምንት ገደማ ብቻ ሲቀረው ነው።

ሚኒስትሯ በተረጋገጠ የፌስቡክ ገጻቸው ያጋሩት ለጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የቀረበ የሥራ መልቀቂያ ደብዳቤ ዛሬ ሰኞ መስከረም 17 ቀን 2014 ዓ.ም የተጻፈ ነው።

ፊርማቸው እና በስማቸው የተቀረጸ የተቋሙ ማሕተም ባረፈበት ደብዳቤ ፊልሰን “በበርካታ አገራዊ እና ተቋማዊ በተለይ የሴቶች ሕፃናት እና ወጣቶች ሚኒስቴር ጉዳዮች” ላይ ከጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ጋር መወያየታቸውን ገልጸዋል።

ፊልሰን በደብዳቤው “በሕሊናዬ ላይ ከባድ ጫና በሚያሳድሩ” ባሏቸው የግል ጉዳዮች ምክንያት ከኃላፊነታቸው ለመልቀቅ መወሰናቸውን ገልጸዋል።

የኢትዮጵያ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የወይዘሮ ፊልሰን አብዱላሒን ሹመት ያጸደቀው በመጋቢት 2012 ዓ.ም. ነበር።

ወደ ፖለቲካ ከመግባታቸው በፊት በሶማሌ ክልል ነበድ የተባለ የግል ቴሌቭዥን አቋቁመው በኃላፊነት መርተዋል።

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትስስር ይፍጠሩ

325,851FansLike
49,039FollowersFollow
13,194SubscribersSubscribe