ሚኒስትሯ በጎዳና ተዳዳሪዎች ስም 400 ሚሊዮን ብር ደረሰኝ ማቅረብ አልቻሉም

የሴቶችና ህፃናት ሚኒስቴር የመስሪያ ቤቱን የሶስት ወራት የፋይናን አፈፃፀም በተመለከተ ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ሰሞኑን አቅርቧል፤

የመንግስት ባለስልጣናት ሙሰኝነቱ በርትቷል። የሴቶች እና ማኅበራዊ ሚኒስቴር በጎዳና ተዳዳሪዎች ስም 400 ሚሊዮን ብር በልቷል።

ከሚኒስትሮቹ ጀምሮ እስከ በታች ባለስልጣናቱ በተቀናጀ መልኩ ለዘረፉት 400 ሚሊዮን ብር ደረሰኝ ማቅረብ አልቻሉም። ይህም በፓርላማው ተረጋግጧል።

ፓርላማው የሴቶች እና ማኅበራዊ ሚኒስቴር ውሎ እና አዳራቸውን በጎዳና ላይ ያደረጉ ሕፃናት እና እናቶችን ለማቋቋም እየሠራ ያለው ሥራ በቂ አይደለም ሲል ገልጿል።

ለጎዳና ትዳዳሪዎች በሚል ከ400 ሚሊዮን ብር በላይ ለክልሎች ተሰራጭቷል ቢባልም የደረሰኝ ማስረጃዎች ግን አልቀረቡም፤ ይህንን ስራ የሚያስረዳ ሰነድ ማቅረብም አልተቻለም።

ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱን የሚመሩት ለኮስሞቲክስ በርካታ ዶላሮችን እንደሚያወጡ የሚነገርላቸው ዶክተር ኤርጌጎ ተስፋየ ናቸው።

ፓርላማው ሚንስቴሩ ሊመራበት የሚገባው የማህበራዊ ፈንድ አዋጅ ከ4 አመት በላይ ሳይጸድቅ መቆየቱ፤ ሚንስቴሩ በ2014 ከ22 ሺህ በላይ የጎዳና ተዳዳሪዋችን ከመንገድ አንስቻለው ባለው አሀዛዊ መረጃ ላይ አመኔታ አላደረብንም ያለ ሲሆን በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ላይ ያሉ ዜጎች ወደ ጎዳና ሳይወጡ መከላከል አለመቻል፣ ከዓለም ባንክ የተገኘው የገንዘብ ድጋፍ በአግባቡ ለታለመለት ዓላማ መዋሉን በቂ ሪፖርት አለማቅረብ፣ በጎዳና ላይ ያሉ ዜጎችን የተመለከተ የመረጃ ቋት አለመኖር እና ለአገልግሎት መስጫ ማገገሚያ ማዕከላት ምን ያህል ገንዘብ እንደተመደበ ትክክለኛ ማስረጃ አለመቅረብ የሚሉት እና ሌሎችም በኦዲት ሪፖርት ቀርበዋል።

ለጎዳና ተዳዳሪዎች በሚል ከ400 ሚሊዮን ብር በላይ ለክልሎች ተሰራጭቷል ቢባልም ማስረጃዎች አልተገኙም ።

የፕላንና ልማት ሚኒስቴር ይህ መሰረታዊ ማህበራዊ ችግር “ከድጡ ወደ ማጡ ሆኗል” ብሏል።

በልዩ ልዩ ችግሮች ተገፍተው ጎዳና ላይ ውለው የሚያድሩ ሕፃናትን እና እናቶችን በማንሳት ወደ ማገገሚያ ማዕከላት ለማስገባት የሚሠሩ የተለያዩ የግል ተቋማት እንዳሉ በሪፖርቱ ተመላክቷል።

ነገር ግን በዚህ መንገድ ብቻ ጎዳና የወደቁ እናቶችን ማንሳት ዘላቂ መፍትሄ ስለማያመጣ መንግስት ዘላቂ ነው ያለውን መፍትሔ እንዲሻ አሳስበዋል።

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትስስር ይፍጠሩ

325,851FansLike
49,039FollowersFollow
13,194SubscribersSubscribe