ሚኪያስ ተፈራ (ሞፈር ቡና) የቢቂላ አዋርድ  2025 የቢዝነስ ልቀት ሽልማት ተመረጠ

ቶሮንቶ፣ ካናዳ — የቢቂላ አዋርድ  የ2025 ተሸላሚዎችን አሳውቋል፡፡  በቶሮንቶ በመጪው መስከረም ለሚከበረው አመታዊ ክብረ በዓል  የላቀ አስተዋፅዖ ያበረከቱ በማኅበረሰባቸው እና ከዚያም በላይ ዘላቂ ተጽእኖ ያደረጉ ግለሰቦችን ያከብራል።

ሚኪያስ ተፈራ (ሞፈር ቡና) ለባለራዕይ ስራ ፈጣሪነት፣ አመራር እና የበጎ አድራጎት አስተዋፅዖ የንግድ ልቀት ሽልማት በመጪው መስከረም ወር  የቢቂላ ሽልማት ከሚበተክትላቸው መሀከል መሆኑ ታውቋል፡፡። ሚልኪያስ የሞፈር ቡና መስራች እና ዋና ስራ አስፈፃሚ ነው፤  ኢትዮጵያዊ-ካናዳዊ ስራ ፈጣሪ  የሆነው ሚኪያስ በማህበረሰብ እና በትውፊት ላይ የተመሰረተ ቡናን በመጠቀም የባህል ንቅናቄን መገንባት ችሏል።

ሞፈር ኮፊ

የቢቂላ ሽልማት አዘጋጆች ባወጡት  ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ ሌሎች  ተሸላሚዎችንም ይፋ አድርገዋል፡፡ በዚህም መሰረት፡-

ሎሬት ጸጋዬ ገብረመድህን  በኢትዮጵያ ሥነ-ጽሑፍ እና የኪነጥበብ ስራዎች ፈር ቀዳጅ አስተዋጾኦ ያበረከቱ በመሆኑ  ልጆቹ ማህሌት እና ዮዲት ፀጋዬ በስሙ ሽልማቱን ይቀበላሉ።

ዶ/ር ደብረወርቅ ዘውዴ — ለአለም አቀፍ ጤና የላቀ አስተዋፅዖ በማበርከቱ የዕድሜ ልክ ስኬት ሽልማት ተሸላሚ።

ኢንጂነር ጌዲዮን አስፋው — በታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ላይ የማማከር ስራዎችን ጨምሮ በውሃ ሃብት አስተዳደር ላስመዘገቡ ውጤቶች ሙያዊ የላቀ ሽልማት ተሸላሚ።

ዶ/ር ኦብሲኔት ሜሪድ እና ዶ/ር ተስፋዬ ተሊላ — በኢትዮጵያ የልብና የደም ህክምና እና የሰብአዊ አገልግሎት አመራር ሙያዊ የላቀ ሽልማት ተሸላሚ።

ዶ/ር ሙሉ ገለቱ – የማህበረሰብ አገልግሎት የልህቀት ሽልማት ተሸላሚ ለወጣቶች ማብቃት እና መካሪ።

  • ዶ/ርቶማስቦጋለ – ለኒውሮቫስኩላር እና የራስ ቅል መሰረት ቀዶ ጥገና፣ የታካሚ እንክብካቤን፣ ምርምርን እና ትምህርትን በማሳደግ የባለሙያ የላቀ ሽልማት ተሸላሚ።
  • ገሊ ላገረመው -በወጣቶች ማህበረሰብ ተፅእኖ አመራር እና ተሳትፎ ተሸላሚ።
  • ሮቤል አዱኛ – በወጣቶች ማህበረሰብ ተፅእኖ ላይ ያተኮሩ ተነሳሽነቶች በመለየት መጪውን ትውልድ በማበረታታት ተሳትፎ ተሸላሚ።
  • ናርዶስ ዋቅጂራ ፣ሃና ፍቅሩ እና እሴቴ መኮንን – ለአካዳሚክ የላቀ ቁርጠኝነት በማሳየት ተሸላሚ፤ ናርዶስ ዋቅጂራ እና ሃና ፍቅሩ በሞፈር ቡና ወጪያቸው ተሸፍኖ የ2025 የቢቂላ ስኮላርሺፕ ያገኛሉ።

ባለፈው አመት ተወዳጁ አርቲስት ቴዲ አፍሮ በቶሮንቶ የቢቅላ ሽልማት የተበረከተለት መሆኑ ይታወሳል።

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትስስር ይፍጠሩ

325,851FansLike
49,039FollowersFollow
13,194SubscribersSubscribe