ማኑዋል መኪና መንዳት የአንጎልን ብቃት እንደሚያሳድግ አዲስ ጥናት አመለከተ

ማኑዋል መኪና መንዳት ለአእምሮ ጤና ከፍተኛ ጠቀሜታ እንዳለው በጃፓን የተደረገ አዲስ ጥናት ጠቆመ።
ጥናቱ እንደሚያመለክተው ማኑዋል መኪናዎችን ማዘውተር ለአውቶማቲክ መኪናዎች ከሚሰጠው ትኩረት ይልቅ የአንጎልን የማስታወስ፣ ትኩረት የመሰብሰብ እና ውሳኔ የመስጠት ብቃት በከፍተኛ ሁኔታ ያነቃቃል።
ይህንን ግኝት ይፋ ያደረጉት በቶሆኩ ዩኒቨርሲቲ ታዋቂው የነርቭ ሳይንቲስት ፕሮፌሰር ርዩታ ካዋሺማ ናቸው።
በምርምራቸው መሠረት፤ ማኑዋል መኪና በሚነዳበት ወቅት የሚፈለጉት እንደ ክላች መርገጥ፣ ማርሽ መቀየር፣ የነዳጅ መቆጣጠሪያን ማስተካከልና የትራፊክ ፍሰትን በአንድ ላይ ማቀናጀት ያሉ ተከታታይ ተግባራት ከፍተኛ የእውቀት ሥራዎችን የሚያከናውነውን የአንጎል የፊት ክፍል ያነቃቁታል።
ይህ በአንድ ጊዜ በርካታ ሥራዎችን የማስተናገድ ሂደት አእምሮ ያለማቋረጥ ንቁ ሆኖ መረጃዎችን እንዲያሰላስል የሚያስገድደው በመሆኑ፣ ለአንጎል ታላቅ የዕለት ተዕለት የስፖርት እንቅስቃሴ ሆኖ ያገለግላል ተብሏል።

SourceBBC News

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትስስር ይፍጠሩ

325,851FansLike
49,039FollowersFollow
13,194SubscribersSubscribe