ምርጫ ቦርድ፤ የወላይታ ዞን ህዝበ ውሳኔን በድጋሚ ለመሰረዝ የሚያስገድዱ ችግሮች አጋጥመውት እንደነበር የቦርዱ ምክትል ሰብሳቢ ተናገሩ!

ድጋሚ በተደረገው የወላይታ ዞን ህዝበ ውሳኔ ላይ፤ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የምርጫ ሂደቱን በድጋሚ “እንዲሰረዝ” የሚያስገድዱ ተግባራት በዞኑ ዋና አስተዳዳሪ ሲፈጸሙ እንደነበር የቦርዱ ምክትል ሰብሳቢ አቶ ውብሸት አየለ ተናገሩ። የወላይታ ዞን ዋና አስተዳዳሪ በህዝበ ውሳኔው ዕለት፤ ምርጫ ቦርድ “ሌላ ውሳኔ እንደሰጠ” አድርገው መልዕክት ሲያስተላልፉ እንደነበርም አቶ ውብሸት ገልጸዋል።

የምርጫ ቦርድ ምክትል ሰብሳቢ ይህንን ያሉት፤ ዛሬ ረቡዕ ሰኔ 28፤ 2015 በተካሄደ የፌዴሬሽን ምክር ቤት መደበኛ ጉባኤ ላይ ተገኝተው በሰጡት ማብራሪያ ነው። አቶ ውብሸት በንባብ ለምክር ቤቱ ባቀረቡት የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ህዝበ ውሳኔ አጠቃላይ ሪፖርት፤ ምርጫ ቦርድ ህዝበ ውሳኔውን ለማካሄድ ያለፋቸውን ሂደቶች፣ የተገኘውን ውጤት እንዲሁም ያጋጠሙትን ችግሮች ዘርዝረዋል።

በ26 ገጾች በተዘጋጀው በዚሁ ሪፖርት ውስጥ በችግርነት ከተጠቀሱ ጉዳዮች ውስጥ፤ በወላይታ ዞን ተከስተው ነበር የተባሉ የህግ ጥሰቶች ይገኙበታል። በወላይታ ዞን ባለፈው ጥር ወር የተካሄደው ህዝበ ውሳኔ እንዲሰረዝ ምክንያት የሆኑ የህግ ጥሰቶችን አጽንኦት ሰጥተው ያነሱት ምክትል ሰብሳቢው፤ ከዚህ ጋር በተያያዘ የተጠረጠሩ 94 ግለሰቦች በቁጥጥር ስር መዋላቸውን ለፌዴሬሽን ምክር ቤት አባላት ተናግረዋል። ምርጫ ቦርድ ሰኔ 12፤ 2015 በወላይታ ዞን በድጋሚ ህዝበ ውሳኔ ሲያካሄድም ችግሮች እንዳጋጠሙት አቶ ውብሸት በዛሬው ሪፖርታቸው ጠቁመዋል።

Via Ethiopia Insider

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትስስር ይፍጠሩ

325,851FansLike
49,039FollowersFollow
13,194SubscribersSubscribe