ምርጫ ቦርድ ለፖለቲካ ፖርቲዎች ድጎማ የጠየቀውን 230 ሚሊዮን ብርን መንግስት ውድቅ አደረገው፤

     የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ምርጫ ቦርድ ለፓለቲካ ፓርቲዎች ድጎማ የጠየቀውን የ230 ሚሊዮን ብር የበጀት ጥያቄ እንዳልተቀበለው ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ  አስታወቀ።

     ቦርዱ ዛሬ ከተለያዩ የፖለቲካ ፓርቲዎች ጋር ባደረገው ውይይት ላይ፣ አገሪቱ ካለችበት ሁኔታ አንጻር ገንዘብ ሚንስቴር ገንዘቡን መመደብ እንደማይችል እንዳሳወቀ ገልጧል።

     በቦርዱ ማቋቋሚያ አዋጅ ላይ ለፖለቲካ ፖርቲዎች ምርጫ ቦርድ የገንዘብ ድጋፍ እንደሚያደርግ ቢደነገግም የመንገስት ወቅታዊ አቋም አዋጁን ለመፈፀም እንዳላስቻለው ታውቋል፤ ሆኖም ቦርዱ ከስድስተኛው ሀገራዊ ምርጫ የቁሳቁስ ሕትመት የተረፈውን 50 ሚሊዮን ብር ለፓርቲዎች ድጎማ እንደመደበ ተናግሯል።

     የፓርቲዎች የድጎማ ቀመር፣ ፓርቲዎቹ በምርጫ ያገኙትን መቀመጫ፣ የሴት እና የአካል ጉዳተኛ አባላት ብዛት እና ያሰባሰቡትን የገንዘብ አቅም መሠረት ያደረገ እንደሆነ የተገለፀ ሲሆን ለሀገር አቀፍ የፖለቲካ ፖርቲዎች 30 ከመቶ  ለክልላዊ ፖርቲዎች 20 ከመቶ መደልደሉ ታውቋል፤

ብልፅግና በሁሉም መለኪያዎች ከፍተኛ ነጥብ ስለሚያስመዘግብ አብዛኛውን ድጎማ ሊወስድ ይችላል በሚል ከተቃዋሚ የፖለቲካ ፖርቲዎች ተቃውሞ ቀርቦበታል።

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትስስር ይፍጠሩ

325,851FansLike
49,039FollowersFollow
13,194SubscribersSubscribe