ምርጫ ቦርድ በምርጫ አስፈጻሚ ምልመላ ላይ የፖሊሲ ለውጥ ማድረጉን ቢገልጽም ይህ ነው የሚባል ለውጥ አለመታየቱን የፖለቲካ ፓርቲዎች ገለጹ

ከአሁን ቀደም ምርጫ ያስፈጸሙ ደግመው በአስፈጻሚነት እንዳይመዘገቡ ከማድረግ ጀምሮ በርካታ ማሻሻያዎችን ማድረጉን የቦርዱ ሊቀመንበር ወይዘሪት ብርቱካን ሚዴቅሳ መግለጻቸው ይታወሳል፡፡

አሐዱም ምርጫ ቦርድ ከምርጫ አስፈጻሚ አካላት ጋር ተያይዞ ያደረገው ማሻሻያ ምን ያህል ለውጥ አምጥቷል ሲል የፖለቲካ ፓርቲዎችን ጠይቋል፡፡

የኢትዮጵያ ዴሞክራቲክ ህብረት ሊቀ-መንበር አቶ ገብሩ በርሔ እንደገለጹት ከምርጫ አስፈጻሚ አባላት ጋር ተያይዞ በቦርዱ በኩል የተወሰኑ መሻሻሎች እንዳሉ ተናግረው የፖለቲካ ፓርቲ አዋጁ ግን አሳሪ ነው ይላሉ፡፡

የእናት ፓርቲ ምክትል ፕሬዝዳንት ዶክተር ሰይፈስላሴ አያሌው በበኩላቸው ምርጫ ቦርድ ማሻሻያ ለማድረግ ጥረት ቢያደርግም በተሰራው ልክ ለውጥ መጥቷል ማለት እንደማቻል ገልጸዋል፡፡

በተለይ አባላትን ማንገላታት ላይ ሰፊ ችግር ሲስልተዋል እንደነበር ተናግረው ለቀጣዩ ስራ መሻሻል የሚገባቸው በርካታ ጉዳዮች እንዳሉ ያነሳሉ፡፡

የዕጩ መምዝገባ መጠናቀቁ የሚታወስ ሲሆን ሂደቱም በበርካታ ፖለቲካ ፓርቲዎች ዘንድ ቅሬታ ያስነሳ እንደነበር የሚዘነጋ አይደለም፡፡

Kumneger Media
Kumneger Media
Kumneger Media is a News and Entertainment Website & Channel. Kumneger Media in addition to News and Entertainment it is the hub of Politics, Movies, Drama, Music, Comedy, Documentary and More!

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትስስር ይፍጠሩ

325,851FansLike
49,039FollowersFollow
13,194SubscribersSubscribe