ምንድነው ነገሩ?

(ርዕሠ አንቀፅ) ከማንም ቀድመው የህብረተሰቡን ችግርና ዕጣ ፈንታ በብዕራቸው ነቅሰው ያወጣሉ ተብለው የሚጠበቁት የኪነጥበብ ባለሙያዎች ሀገሪቱ በአራቱም ማዕዘናት በጦርነትና በጦር ወሬ በተያዘችብት በዚህ ወቅት አልሰማንም አላየንም ማለታቸው ለምን ይሆን?
ህዝቡ በጦርነቱ ሳቢያ ከተወለደበትና ካደገበት ቀዬ ሲፈናቀል የሚበላውና የሚቀምሰው አጥቶ የእርዳታ ያለህ በሚልበት በዚህ ወቅት ሀብቴ ህዝቤ ነው የሚሉት የኪነ ጥበብ ባለሙያዎች በየመድረኩ እየተገኙ ለህዝቡ ሳይሆን ለመንግስት ባለስልጣና ወዳሴ ማቅረባቸው ለምን ይሆን?
የአንድ እናት ልጆች በለኮሱት ጦርነት ሳቢያ ሰላም ሲጠፋና የሰላም አየር ለመተንፈስ ህዝቡ ሲማፀን ጦር መስበቅና ዘገር መነቅነቅን የሚያደፋፍሩ ጥበበኞች የምንምለከትው ለምን ይሆን?
ህብረተሰቡን የሚያንፅ የፈጠራ ስራዎችን በመስራት የመንፈስ ምግብ ይመግባሉ ተብለው የሚጠበቁ ሙያተኞቹ ከፊት ከመቀደም ይልቅ የኋላ ሰልፈኞች ሆነው የመንግስትን አጀንዳ ብቻ እየተከተሉ ሲያላዝኑ የምንመለከታቸው ለምን ይሆን?
ከራሳቸው አልፈው ሌሎች ወገኖቻቸውን ከኢኮኖሚያዊ ጉስቁልናና ችግር ይታደጋሉ ተብለው ተስፋ የተጣለባቸው አርቲስቶችን ለህመማቸውም ሆነ ለቀብራቸው (ለሀውልታቸውም ጭምር) በተደጋጋሚ ህዝባዊ ቴሌቶን ሲዘገጅላቸው የምንመለከተው ለምን ይሆን? እየተመለከትን ነው፡፡
ራሳቸውንና ሙያቸውን የሚያከብሩ ሙያተኞች በየዘርፉ በመጥፋታቸው ሀገራችን በእጃቸው ላይ ያለው ሙያ ከሚሊዮን ብር በላይ መሆኑን በማያውቁ ‹‹ዝነኞች›› ተሞልታለች፡፡ የተነሳ ሙያተኞቹ የፈጠራ ስራዎቻቸው ተጠቃሚ የሚሆኑበትን አዋጅ ደንብና መመሪያ
መንግስት እስከሚያቀርብላቸው ድረስ የሚጠብቁ ‹‹ጥበበኞች›› መድረኩን ሞልተውት የምንመለከተው ለምን ይሆን?

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትስስር ይፍጠሩ

325,851FansLike
49,039FollowersFollow
13,194SubscribersSubscribe