ምክር ቤቱ የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት የቦርድ አባላትን ሹመት አጸደቀ

የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ዛሬ ባካሄደው መደበኛ ስብሰባ የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት የቦርድ አባላት ሹመትን መርምሮ አጸደቀ፡፡

ዚህም መሰረትም 1. ዶክተር አብርሃም በላይ – ሰብሳቢ

2. ዶክተር ቢቂላ ሁሪሳ – አባል

3. አቶ ጣሂር መሐመድ – አባል

4. ረዳት ፕሮፌሰር መኩሪያ መካሻ – አባል

5. ወይዘሮ ሰሃርላ አብዱላሂ – አባል

6. አቶ አብነት ዘርፉ – አባል

7. አቶ ሰይፈ ደርቤ – አባልና ፀሀፊ ሆነው በሙሉ ድምፅ በምክር ቤቱ ተሹመዋል፡፡

የቦርድ አባላቱ ሹመት ኢዜአ ተልዕኮውን በተሻለ ሁኔታ በብቃት ለመወጣትና ስራዎቹን ወደ ተሻለ ደረጃ ለማሳደግ እንደሚያግዘው ተጠቅሷል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ኤጀንሲ ተጠሪነቱ ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ሆኖ በአዋጅ ቁጥር 1115/2011 እንደገና መቋቋሙ ይታወሳል።

Sourceኢዜአ
Kumneger Media
Kumneger Media
Kumneger Media is a News and Entertainment Website & Channel. Kumneger Media in addition to News and Entertainment it is the hub of Politics, Movies, Drama, Music, Comedy, Documentary and More!

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትስስር ይፍጠሩ

325,851FansLike
49,039FollowersFollow
13,194SubscribersSubscribe