ህንድ ሦስት ሀገራት ብቻ እየሰሩት የሚገኙትን ተዋጊ ጄት ከሩሲያ በመግዛት ልትታጠቅ ነው ተባለ፡፡
ኒውዴሊ የአምስተኛው ትውልድ የተባሉትን እጅግ ዘመናዊ ተዋጊ ጄቶችን የመግዛት ፍላጎት አሳይታለች ነው የተባለው፡፡
ሩሲያ ሰሞኑን እነዚህን ተዋጊ ጄቶች በዱባይ ኤር ሾው ላይ ይዘው ቀርባ ለዓለም አሳይታለች፡፡
ዩናይትድ ስቴትስ ኤፍ 35 የተባለውን ዘመናዊ ተዋጊ ጄት ስትሰራ፡ቻይና ጄ20 እና ጄ35 የሚሰኙትን የምታመርት ሲሆን ሩሲያ ደግሞ ሱ57 የተሰኙ የአምስተኛው ትውልድ ተዋጊ ጄቶችን ታመርታለች፡፡
ሪፖርቶች እንደሚያመላክትቱት የህንድ ባላንጣና ጎረቤት የሆነችው ፓኪስታን ከእነዚህ ዘመናዊ ተዋጊ ጄቶች ውስጥ የቻይናውን ለመግዛት ጥረት ላይ እንደሆነች ተነግሯል፡፡
ይህ የኢስላማባድ ውሳኔም ህንድንም ለሸመታው እንድትዘጋጅ እንዲገፋት እንዳደረጋትም ተሰምቷል፡፡
በህንድ ኤክስፐርቶች መካከል ከፍተኛ ውዝግብ ማስነሳቱ የተነገረ ሲሆን አንዳንዶች ህንድ የራሷን አምስተኛ ትውልድ ጄት በመስራት መታጠቅ ይኖርባታል ሲሉ ሌሎች ደግሞ ለጊዜው በመግዛት መታጠቁ አስፈላጊ ነው ማለታቸው ተሰምቷል፡፡
ሩሲያ እነዚህን ተዋጊ ጄቶች ለሚገዙ ሀገራት የቴክኖሎጂ እና የረጀም ጊዜ ድጋፍ እንደምታደርግ አስታውቃለች፡፡
ፕሬዝዳንት ፑቲን በቀጣዩ ወር መጀመሪያ ሳምንት ወደ ህንድ ጉዞ ያደርጋሉ ተባለ፡፡ ይሔው የፕሬዝዳንቱ ጉዞ የዩክሬኑ ጦርነት ከተመጀረ ወዲህ ወደ ህንድ የመጀመሪያቸው ይሆናል ተብሏል፡፡
የህንዱ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጄ ሻንከር ሰኞ እለት ለሦስት ቀናት ወደ ሞስኮ ማምራታቸው ተሰምቷል፡፡//

