ሩሲያ ኢንተርኔትን ለማቋርጥ እያሰበች ነው

ሩሲያ እራሷን በኢንተርኔት አማካይነት ከሚፈጸም ጥቃት ለመከላከል በምታደርገው ዝግጅት ለአጭር ጊዜ እራሷን ከዓለም አቀፉ የኢንትርኔት ትስስር የማቋረጥ አማራጭን እያጤነች ነው።

ይህም ማለት የኢንትርኔት ግነኙነት በሃገር ውስጥ ብቻ የተገደበ ይሆናል። በዚህም ሩሲያዊያን የሚልኩት እና የሚቀበሉት መረጃ እርስ በርሳው እንጂ ከተቀረው ዓለም ጋር አይሆንም።

ለሙከራው የተቆረጠ ቀን ባይኖርም በቀጣዮቹ ሁለት ሳምንታት ውስጥ እንደሚከናወን ይጠበቃል።

የተቀሩት የዓለም ሃገራት ሩሲያን ከዓለም አቀፉ የኢንተርኔት አገልግሎት ቢያገሏት በእራሷ መቋቋም የሚያስችላት ረቂቅ አሰራር እየተገበረች ነው።

የሰሜን አትላንቲክ የጦር ቃልኪዳን ድርጅት (ኔቶ) ከዚህ ቀደም ሩሲያ የሳይበር ጥቃቶችን ታደርሳለች በማለት ማዕቀብ እንደሚጣልባት ማስጠንቀቂያ ሰጥቷል።

ሩሲያ እንዴት ከተቀረው ዓለም የኢንተርኔት ትስስር እራሷን በማግለል በሃገሪቱ ውስጥ ብቻ የኢንተርኔት አገልግሎትን ማኖር ትችላለች? የሚለው የበርካቶች ጥያቄ ነው።

የዘርፉ በለሙያዎች ሲያስረዱ፤ “ኢንተርኔት የሚሰራበትን መንገድ መረዳት ይገባናል” ይላሉ። “በሺህዎች የሚቆጠሩ መረጃዎች የሚተላለፉባቸው ዲጂታል ኔትዎርኮች አሉ። እንዚህ ኔትወርኮች ‘ራውተር’ በሚባሉ መዳረሻዎች ይገናኛሉ። ሩሲያ ያቀደችው በራውተሮች በኩል ወደ ሃገር ውስጥ የሚገቡ እና የሚወጡ ዳታዎችን መቆጣጠር ነው።”

ይህን አካሄድ በመጠቀም ወደ ሃገር ውስጥ የሚገቡ መረጃዎችን በመቆጣጠር ረገድ ቻይና ውጤታማ ስለመሆኗ ይነገራል።

ሆን ተብሎም ባይሆን ሃገራት በተለያዩ አጋጣሚዎች ከተቀረው ዓለም ጋር የሚኖራቸው የኢንተርኔት አገልግሎት ከዚህ ቀደም ተቋርጧል። ባህር ውስጥ ያለ የኢንተርኔት ገመድ በመቋረጡ ከዚህ ቀደም አፍሪካዊቷ ሃገር ሞሪታኒያ ለሁለት ቀናት ከተቀረው ዓለም ተነጥላ ነበር።

Sourceቢቢሲ
Kumneger Media
Kumneger Media
Kumneger Media is a News and Entertainment Website & Channel. Kumneger Media in addition to News and Entertainment it is the hub of Politics, Movies, Drama, Music, Comedy, Documentary and More!

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትስስር ይፍጠሩ

325,851FansLike
49,039FollowersFollow
13,194SubscribersSubscribe