ሩሲያ የካንሰር ክትባቶችን ለታካሚዎች ለማድረስ መቃረቧን ፕሬዝዳንት ፑቲን አስታወቁ

 የሩሲያው ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን ሩሲያ የካንሰር ክትባቶችን ሰርቶ ለማቅረብ በሂደት ላይ መሆኗንና በቅርቡም ለታካሚዎች ተደራሽ እንደሚሆኑ ገለጹ።
ፕሬዝዳንቱ የካንሰር ክትባቶችን እና የመጪው ትውልድ ሲሉ የገለጿቸውን የሰውነት በሽታ መከላከያን የሚያክሙ (immunomodulatory) መድኃኒቶችን በማዘጋጀት ረገድ ትልቅ ምዕራፍ ላይ ደርሰናል ሲሉ ገልጸዋል።
ፑቲን በሞስኮ ፎረም ላይ አዳዲስ ቴክኖሎጂዎችን በተመለከተ በተዘጋጀ መድረክ ላይ ባደረጉት ንግግራቸው የክትባቶቹ ዝግጅት አሁን ማሳካት የቻሉት ግለሰባዊ የካንሰር ሕክምና (personalised cancer treatments) ደረጃን በቅርቡ እውን ለማድረግ በሚያስችል ሁኔታ ላይ መደረሱን ጠቁመዋል።
ክትባቶቹ የትኞቹን የካንሰር ዓይነቶች እንደሚመለከትም ሆነ የአሰራር ዘዴዎቹን የተመለከተ ዝርዝር መረጃ ባይሰጡም በተመሳሳይ ጥረት ውስጥ በርካታ ሀገራት እና ተቋማት መሰል ክትባቶችን ለማዘጋጀት ከፍተኛ የምርምር ተግባራት በማከናወን ላይ እንደሚገኙ ተገልጿል።
ለአብነትም ባለፈው ዓመት የብሪታኒያ መንግስት በ2030 ለ10 ሺሕ ታካሚዎች ክሊኒካል ሙከራዎች ለማድረግ በማቀድ መቀመጫውን በጀርመን ካደረገው ባዮኤንቴክ ጋር ስምምነት መፈረሙ ይታወሳል።
ከዚህ በተጨማሪም እንደ ሞደርና እና ሜርኽ ያሉ ግዙፍ የመድኃኒት አምራች ኩባንያዎች የካንሰር ሙከራ ክትባቶችን በማዘጋጀት ላይ መሆናቸውን ርይተርስ ዘግቧል።
ሩሲያ በዓለም አቀፉ የኮቪድ-19 ወረርሽኝ መሀል በተለይም ስፑትኒክ ቪ የተሰኘውን ክትባት አዘጋጅታ ለበርካታ ሀገራት ማሰራጨቷን የጠቆመው ዘገባ የክትባቱን ውጤታማነትና ደህንነት ለማመላከት ፑቲን ራሳቸው ስፑትኒክ – ቪ ክትባት በመውሰድ አሳይተዋል ብሏል።
የፕሬዝዳንት ፑቲን መግለጫም የተሻሻሉ የካንሰር ሕክምና አማራጮች ተደራሽ የሚሆኑበትን ተስፋ ለመላው ዓለም የፈነጠቀ ነው ብሎታል።

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትስስር ይፍጠሩ

325,851FansLike
49,039FollowersFollow
13,194SubscribersSubscribe