ሩሲያ የዩክሬን የወደብ ከተማ የሆነችውን ማሪፖል ሙሉ በሙሉ ተቆጣጠረች

የሩሲያ ወታደሮች የዩክሬን የወደብ ከተማ የሆነችውን ማሪፖል ሙሉ በሙሉ መቆጣጠራቸውን የአገሪቱ መከላከያ ሚኒስቴር አስታውቋል፡፡
የሚኒስቴሩ ቃል አቀባይ ኢጎር ኮናሸንኮቭ እንደገለጹት÷ ስትራቴጂያዊ ጠቀሜታዋ ከፍተኛ የሆነችውን የዩክሬን ወደብ ከተማ ማሪፖልን ለመቆጣጠር ለአንድ ወር ያክል ጊዜ የተደረገው ውጊያ በድል ተጠናቋል፡፡
ቃል አቀባዩ በማሪፖል ከተማ አቅራቢያ በሚገኘው አዞቭስታል የተሰኘው ብረት ፋብሪካ ውስጥ መሽገው ሲዋጉ የቆዩ 531 የዩክሬን የመጨረሻ ወታደሮች ለሩሲያ እጅ መስጠታቸውን አረጋግጠዋል፡፡
ይህን ተከትሎም የሩሲያ ወታደሮች የዩክሬን የወደብ ከተማ የሆነችውን ማሪፖል እና አዞቭስታል የብረት ፋብሪካን ሙሉ በሙሉ መቆጣጠር መቻላቸውን ነው የገለጹት፡፡
የዩክሬን ፕሬዚዳን ቮሎድሚር ዘለንስኪ በአዞቭስታል የብረት ፋብሪካ የሩሲያን ጦር ሲመክቱ የነበሩ የአገሪ ወታደሮች ስፍራውን ለቀው እንዲወጡ ትዕዛዝ ሰጥተው እንደነበርም ሞስኮ ታይምስ በዘገባው አስፍሯል፡፡
የሩሲያ ጦርም አካባቢውን በአስተማማኝ ሁኔታ ሙሉ ለሙሉ ለመቆጣጠር በአየር አና በምድር ጦር የታገዘ ዘመቻ ማካሄዱ ተመላክቷል፡፡

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትስስር ይፍጠሩ

325,851FansLike
49,039FollowersFollow
13,194SubscribersSubscribe