ሩሲያ ፕሬዝዳንት ማክሮን በአፍሪካ የሽብር ተግባርን እየደገፉ ነው ስትል ከሰሰች

ሞስኮ በዚህ ወቅት የበርከታ የአፍሪካ ሀገራት የደህንነት ቁልፍ አጋር ስትሆን በተለይም ከሳህል ሀገራት ጋር ያላት ግንኙነት ግን የጠበቀ እንደሆነ ይታመናል፡፡

ሞስኮ ፓሪስ አፍሪካን እንዳትረጋጋ ለማድረግ የሽብር ቡድኖችን ትደግፋለች ስትል ክሷን አሰምታለች፡፡ የሩሲያ ኢንተለጀንስ ፓሪስ አዲስ ቅኝ አገዛዝ በአፍሪካ ለማድረግ በዝጅት ላይ ነች ማለቱን ታስ የተሰኘው የሩሲያ መገናኛ ብዙሃን ዘግቧል፡፡

ይሄው የሩሲያ የኢንተለጀንስ መረጃ የፕሬዝዳንት ኢማኑኤል ማክሮን አስተዳደር ፖለቲካዊ በቀል በአፍሪካ ለማድረግ በዝግጅት ላይ መሆኑን አመላክቷል፡፡

ፕሬዝዳንት ማክሮን አሜሪካ በቬንዙዌላ ኒኮላስ ማድሮን ከስልጣን አንስታ ወደ ኒውዮርክ እስር ቤት እንደወሰደችው ሁሉ በአፍሪካም አንዳንድ መሪዎችን በዚህ መንገድ ማስወገድ ይፈልጋሉ ስትል ሞስኮ ገልጻለች፡፡

ፈረንሳይ በአፍሪካ በተለይም የሳህል እስቴት የቀድሞ የቀኝ ገዥ ነች፡፡

ባለፉት ሁለት እና ሦስት ዓመታት በቀጠናው በነበረው የመንግስት ለውጥ ተከትሎ የሳህል ሀገራት ከፈረንሳይ ጋር የነበራቸውን ግንኙነት ሙሉ በሙሉ አቋርጠው ፊታቸውን ወደ ሞስኮ አዙረዋል፡፡

ማሊ፡ኒጀር እና ቡርኪናፋሶ ተጠቃሾቹ ናቸው፡፡ ሦስቱም የሳህል ሀገራት ከ2020 እስከ 2023 ባሉት ዓመታት ውስጥ ከባድ የሚባል እና ተደጋጋሚ የመንግስት ግልበጣ ተደርጎባቸዋል፡፡ ሦስቱም ሀገራት ከኢኮዋስ እራሰቸውን አግልለው የራሳቸውን የሳህል እስቴት ጥምረት የተሰኘ አዲስህ ውህደትም ፈጥረዋል፡፡

ለዚህ አዲስ ጥምረት መፈጠርም እንደ ምክንያት ያነሱት ሉዓላዊነታችን እንዲከበር እንፈልጋለን የምዕራቡ የእጅ አዙር አገዛዝንም ከዚህ በላይ መታገስ ይበቃናል የሚል ነው፡፡

ከምዕራቡ ሀገራትም ጋርም የጎንዮሽ የሚታያዩበት መንፈስ ከተፈጠረ ዋል አደር ብሏል፡፡ በዚህ መሠረትም በቡርኪናፋሶው ፕሬዝዳንት ኢብራሂም ትራውሬ እስካሁን ከ20 በላይ የግድያ ሙከራ እንደተደረገባቸው የሚያሳዩ የተለያዩ ሪፖርቶች በተደጋጋሚ ወጥተዋል፡፡

በእነዚህ የግድያ ሙከራዎች ውስጥም ፈረንሳይ እጇ እንዳለበት ሞስኮ ከመናገር አልሸሸገችም፡፡ በተጠናቀቀው የጥር ወር በትራውራሬ ላይ ተሞክሮ በነበረው የግድያ ሙከራ ፈረንሳይ እንዳለችበት የሩሲያ ኢንተለጀንስ ይፋ አድርጓል፡፡

ፓሪስ ከዚህ ቀደም በአፍሪካ የነበራትን ሚና በማጣቷ ፖለቲካዊ የበቀል እርምጃ ለመውሰድ በሚል የሽብር  ቡድኖችን እየደገፈች የሚል ክስ ነው ሞስኮ ያቀረበችው፡፡

ይሔው ተመሳሳዩ ሙከራም በፕሬዝዳንት አስሚ ጎይታም ሆነ በፕሬዝዳንት አል ታኒ እንደተሞከረ ነው የገለጸችው፡፡

ፓሪስ እስካሁን በሞስኮ ለቀረቡባት ለእነዚህ ክሶች የሰጠችው ይፋዊ ምላሽም ሆነ ማስተባበያ የለም፡፡

በዚህ ስዓት አፍሪካ የሩሲያ እና የምዕራቡ ሀገራት የሃይል ፉክክር ማዕከል ስለመሆኗ እየተነገረ ነው፡፡//

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትስስር ይፍጠሩ

325,851FansLike
49,039FollowersFollow
13,194SubscribersSubscribe