ሩስያ በይፋ ከአውሮፓ ምክር ቤት ጋር ተፋታች

ሩስያ ከድርጅቱ መውጣቷን ለአውሮፓ ምክር ቤት በይፋ አሳውቃለች።

የሩስያ ዱማ ምክትል አፈጉባዔ ፒዮትር ቶልስቶይ ዛሬ ማክሰኞ እንዳስታወቁት ከሆነ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሰርጌ ላቭሮቭ ደብዳቤ ለድርጅቱ ዋና ፀሃፊ ተላልፏል።

” ከአውሮፓ ምክር ቤት ጋር የሚደረገውን ውይይት ለማቋረጡ ሁሉም ሃላፊነት በNATO አባል ሀገራት ላይ ነው ” ያሉት ቶልስቶይ ” ይህን ሁሉ ጊዜ በሰብአዊ መብቶች ርዕስ የራሳቸውን ጂኦፖለቲካዊ ፍላጎቶች ለማሟላት እና በሀገራችን ላይ ለሚሰነዘሩ ጥቃቶች ሲጠቀሙበት ቆይተዋል ” ብለዋል።

አክለውም ፤ ” ከዚህ በፊት ታይቶ በማይታወቅ መልኩ በተጣለው ማዕቀብና በፖለቲካዊ ጫናዎች ” ምክንያት ሩስያ ዓመታዊውን ክፍያ ለአውሮፓ ም/ቤት አትከፍልም ሲሉ አሳውቀዋል።

ቶልስቶይ ሩሲያ ድርጅቱን ለቃ የምትወጣው ” በራሷ ፈቃድ ” እንደሆነ ገልፀው ውሳኔው ሚዛናዊ እና የታሰበት ነው ብለዋል።

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትስስር ይፍጠሩ

325,851FansLike
49,039FollowersFollow
13,194SubscribersSubscribe