መገናኛ ብዙሃን ለሙዚቀኞች የሮያሊቲ ክፍያ እንዲከፍሉ የሚያስገድደው መመሪያ ከሀምሌ 1 ጀምሮ ወደ ስራ ይገባል ተብሏል፡፡ የሮያሊቲ ክፍያ ረቂቅ መመሪያውን ለማስፈጸም ስልጣን የተሰጠው የኢትዮጽያ አዕምሯዊ ንብረት ባለስልጣን ነው፡፡
እነዚሁ ጣቢያዎች የሚያጫዊቷቸውን ሙዚቃዎች የሚመዘግብ ዌብሳይትም ይፋ ሆኗል፡፡ የሮያሊቲ ክፍያ ጉዳይ ከ20 ዓመት በፊት ጀምሮ ሲነሳ የቆየ ነገር ግን እስከ ዛሬ ድረስ ተግባራዊ ሳይሆን የመጣ ነው፡፡
ሙዚቀኞች በዘፈኖቻቸው ክፍያ ለማግኘትም ስራዎቻቸውን በዌብሳይቱ ላይ ማስመዝገብ ይኖርባቸዋል፡፡ ህይወታቸው ያለፈ ሙዚቀኞችን በሚመለከት የሟች ወራሾች ገቢውን እንዲገኙ መመሪያው ያደርጋል መባሉም ተሰምቷል፡፡
በታዋቂው ሙዚቃ አቀናባሪ ኤሊያስ መልካ ስም የተሰየመው EMCCMO.COM የተሰኘው ይህ ዌብሳይት ባለቤትነታቸው የተረጋገጡ የድምጻዊያን ስራዎችን ይመዘግባል ነው የተባለው፡፡
ዌብሳይቱ በሚዲያዎች በ24 ስዓት ውስጥ ምን ያህል ሙዚቃ እንደተላለፈ የሚመዘግብበትን ስርዓትም አካቷል ተብሏል፡፡
ይህም መገናኛ ብዙሃን በሚያጫውቷቸው ሙዚቃዎች ለሚከፍሉት የሮያሊት ክፍያ መረጃን የሚሰጥ ይሆናል፡፡
የኢትዮጽያ የቅጅና ተዛማጅ መብቶች የጋራ አስተዳደር እና የኢትዮጽያ የሙዚቃ እቅጅና ተዛማጅ መብቶች የጋራ አስተዳደር ባደረጉት ውይይት ነው ይህ የተሰማው፡፡
በኢትዮጽያ የቅጅና ተዛማጅ መብቶች ጥበቃ ባለመደረጉ የስራው ባለቤች እንዳይጠቀሙ አድርጓቸው እንደቆየም ይነሳል፡፡

