ሮናልዶ በተከታታይ ለ21 ዓመታት ለብሔራዊ ቡድኑ ግብ ማስቆጠር የቻለ በታሪክ የመጀመሪያው ተጨዋች መሆኑ ታወቀ

ሮናልዶ “እኔ ክብረወሰኖችን አላሳድድም ክብረወሰኖች ራሳቸው ያሳድዱኛል” ማለቱ ይታወቃል

ፖርቹጋላዊው የፊት መስመር ተጨዋች ክርስቲያኖ ሮናልዶ በዓለም የእግር ኳስ መድረክ አዳዲስ ታሪኮችን እና ክብረወሰኖችን ማስመዝገቡን እንደቀጠለ ነው።

ከዚህ ቀደም “እኔ ክብረወሰኖችን አላሳድድም ክብረወሰኖች ራሳቸው ያሳድዱኛል” ያለው የ39 ዓመቱ ሮናልዶ፤ አሁንም አዳዲስ ክብረወሰኖችን በእጁ ማስገባቱን ቀጥሏል።

ባሳለፍነው ማክሰኞ ፖርቹጋል ከአየርላንድ ጋር ያደረገችውን የወዳጅነት ጨዋታ 3ለ0 በሆነ ውጤት ባሸነፈችበት ጨዋታ ላይ ሁለት ግቦችን ከመረብ ያሳረፈው ክርስቲያኖ ሮናልዶ፤ በእለቱ አዲስ ክብረወሰን በእጁ አስገብቷል።

በዚህም ፖርቹጋላዊው የፊት መስመር ተጨዋች ክርስቲያኖ ሮናልዶ በተከታታይ ለ21 ዓመታት ለብሔራዊ ቡድኑ ግብ ማስቆጠር የቻለ በታሪክ የመጀመሪያው ተጨዋች መሆን ችሏል።

ክርስቲያኖ ሮናልዶ በፈረንጆቹ ከ2004 ጀምሮ ላለፉት 21 ዓመታት በየዓመቱ ለፖርቹጋል ብሔራዊ ቡድን ግቦችን ማስቆጠር የቻለ ሲሆን፤ ሮናልዶ ለፖርቹጋል ብሔራዊ ቡድን ያስቆጠራቸውን ግቦች 130 አድርሷል።

በእግር ኳስ ዘመኑ ከ890 በላይ ግቦችን ያስቆጠረ ሲሆን፤ ከፖርቹጋል ብሄራዊ ቡድን እና ከተለያዩ ክልበቾ ጋር በመሆንም ከ32 በላይ ዋንጫዎችን ማንሳት ችሏል።

ሮናልዶ በእጁ ያስገባቸው ክብረወሰኖች የትኞቹ ናቸው?

– ፖርቹጋላዊው የፊት መስመር ተጨዋች ክርስቲያኖ ሮናልዶ በፈረንጆቹ 2021 ላይ በ201 ጨዋታዎች ተሰልፎ ላይ ከ130 በላይ ግቦችን በማስቆጠር በአሊ ዳኤይ ተይዞ የነበረውን ክብረወሰን በእጁ አስገባ።

– ሮናልዶ ለፖርቹጋል ከ200 በላይ ጨዋታዎች ላይ ተሰልፎ መጫወት ችሏል

– ክሪስቲያኖ ሮናልዶ በወንዶች እግር ኳስ ለብሔራዊ ቡድን በርካታ ጊዜ የተሰለፈ ተጫዋቾች በመሆን በኩዌቱ አጥቂ ባድር አል-ሙታዋ ተይዞ የነበረውን ክብረወሰን በፈረንጆቹ 2023 በእጁ አስገብቷል።

– በዩሮ ማጣሪያ ከሊችተንስታይን ጋር በተደረገው ጨዋታ ሮናልዶ 130ኛ ዓለም አቀፍ ግን ያስቆጠረው ክርስቲያኖ በዚህም የመጀመሪያው ተጫዋች ሆኗል።

– በፈረንጆቹ ከ2004 እና 2022 መካከል በ11 ተከታታይ አለም አቀፍ ውድድሮች ላይ ጎል ያስቆጠረ ብቸኛው ተጫዋች ነው።

– ፖርቹጋላዊው የፊት መስመር ተጨዋች ክርስቲያኖ ሮናልዶ በ5 የዓለም ዋንጫዎች ላይ ግብ ያስቆጠረ ብቸኛው ተጫዋች ሲሆን፤ በ5 የዓለም ዋጫዎች ላይ በተከታታይ ከተጫወቱ 5 ተጫዋቾች መካከልም አንዱ ነው።

– በዓለም ዋንጫ ላይ በ21 ዓመት ጎብ በማስቆጠር የፖርቹጋል በእድሜ ትንሹ ግብ አስቆጣሪ እንዲሁም በ37 ዓመቱ ግብ በማስቆጠር በእድሜ ትልቁ የዓለም ዋንጫ ግብ አስቆጣሪ ነው።

– በ2017 ብቻ 32 ዓለም አቀፍ ግቦችን በማስቆጠር (ለክለብ እና ለብሄራዊ ቡደን) በአንድ የውድድር ዘመን በርካታ ግቦችን በማስቆጠር የቻል ብቸኛ ተጫዋች ነው ።

በአውሮፓ

– በአውሮፓ ሻፒየንስ ሊግ ለሶስት የተለያዩ ክለቦች ከ10 በላይ ግቦችን ማስቆጠር የቻለ ብቸኛ ተጫዋች ነው።

– ሮናልዶ በአውሮፓ ቻምፒየንስ ሊግ ታሪክ 141 ግቦችን በማስቆጠር የቻለ ተጫዋች ሲሆን፤ ከሚሲ በ12 ግቦች ይበልጣል፤ ሜሲ ሮናልዶ በአውሮፓ ቻምፒየንስ ሊግ ያስቆጠራቸው ግቦች 129 ናቸው።

– የአውሮፓ ሻምፒየንስ ሊግ ዋንጫ ከፍተኛ ግብ አግቢነት ክብረወሰንን በ2013/14 የውድድር ዘመን ላይ 17 ግቦችን በማስቆጠር ሰብሯል።

– ሮናዶ በ4 የቻምፒየንስ ሊግ የፍጻሜ ጨዋታዎች ላይ ግብ በማስቆጠር የሚስተካከለው ተጨዋች የለም።

በማንቸስተር ዩናይትድ

– ሮናልዶ በ2007/8 የውድድር ዓመት የዓመቱ ምርጥ ተጫዋች እና የዓመቱ ወጣት ተጫዋች የሚሉ ሁለት ሽልማቶችን በአንድ ጊዜ አሸንፏል።

– ሮናልዶ የማንቸስተር ዩናይትድ በአንድ የውድድር ዘምን ከፍተኛ ግብ አስቆጣሪነት ክብረ ወሰንን በ31 ግቦች ይዟል።

– በ2009 ፖሮቶ ላይ ባስቆጠራት ልዩ ግብ የፑሽከሽ ሽልመታን ማሸነፍ የቻል የመጀመሪያው እና ብቸኛው የማቸስተር ዩናይትድ ተጫዋች ነው

– ሮናልዶ በረፈንጆቹ 2008 የአውሮፓ የወርቅ ጫማ ያሸነፈ ብቸኛው የምንቸስተር ዩናይትድ ተጫዋች ነው።

– ሮናልዶ በ2008 ላይ የዓለመ ምርጥ ተጫዋች ተብሎ የተሸለመ ብቸኛው የማንስተር ዩናይትድ ተጫዋች ነው።

ሪያል ማድሪድ

– ሮናልዶ በተከታታይ ከ50 በላይ ጎሎችን በማስቆጠር ሪከርድ የሰበረ ሲሆን፤ ይህንንም ያሳካው በፈረንጆቹ ከ2011 እስከ 2016 ባሉ የወድድር ዘመን ነው።

– በሪያል ማድሪድ ታሪክ ከፍተኛ ግብ አስቆጣሪ ሲሆን፤ ለሪያል ማድሪድ 438 ጨዋታዎች ላይ ተሰልፎ 451 ግቦችን ከመረብ አሳርፏል።

– በስፔን ላሊጋ ታሪክ በአንድ ጨዋታ ላይ 3 እና ከዚያ በላይ ግቦችን ማስቆጠር የቻለ ብቸኛ ተጫዋች ሲሆን፤ በዚህም ሮናዶ በ34 ጨዋታዎች ላይ 3 እና ከዚያ በላይ ግቦችን ማስቆጠር ችሏል።

– ለሪያል ማድሪድ በ2014/15 የውድድር ዘመን 61 ግቦችን በማስቆጠር በክለቡ ታሪክ ብቸኛው እና የመጀመሪያው ተጫዋች ነው።

ጁቬንቱስ

– ሮናልዶ በጣሊያን ሴሪ አ በፈረንጆቹ 2019/20 የውድድር ዘመን ለጁቬንቱስ በአንድ የውድድር ዘመን 37 ግቦችን በማስቆጠር የክለቡን ከፍተኛ ግብ አስቆጣሪነግ ክብረ ወሰን በእጁ አስግበቷል።

– ሮናልዶ በፕሪምየር ሊግ፣ በላሊጋ እና በሴሪያ ከ50 በላይ ግቦችን በማስቆጠር የመጀመሪያው ተጫዋች ሆኗል

– በአውሮፓ 5 ከፍተኛ ሊጎች ውስጥ 30 እና ከዚያ በላይ ግቦችን ማስቆጠር የቻለ ብቸኛው ተጫዋች ነው።

– በ2020 በካግሊያሪ ላይ 3 ግቦችን በማስቆጠርም፤ በጣሊያን ሴሪ አ ታሪክ ሃትሪክ መስራት የቻለ የመጀመሪያው ፖርቹጋላዊ ለመሆን በቅቷል

– በፕሪምየር ሊግ፣ በላሊጋ እና በሴሪያ ሃሪክ መስራ ከቻሉ ሁለት ተጫዋቾች አንዱ ሲሆን፤ ይህንን ክብረወሰንም ከዝላታን ኢብራሂሞቪች ጋር ተጋርቷል።

ሳዑዲ አረቢያ (አል ናስር)

ለሳዑዲ አረቢያው አል ናሰር የሚጫወተው ክርስቲያኖ ሮናልዶ የዘንዶሮ የሳዑዲ ፕሮ ሊግ ከፍተኛ ግብ አስቆጣሪ ሲሆን፤ በ31 ጨዋታ 35 ጎሎች መረብ ላይ ማሳረፍ ችሏል።

በዚህም ሮናልዶ በሳውዲ ሊግ በአንድ የውድድር አመት ብዙ ጎል በማስቆጠር አዲስ ክብረ ወሰን አስመዝግቧል።

ሮናልዶ በፈረንቹ 2019/20 በሞሮኳዊው ተጫዋች በ34 ግብ ተይዞ የነበረው የአንድ የውድድር ዘመን ከፍተኛ ግብ አስቆጣሪነት ክብረወሰንን በእጁ አስገብቷል።

ይህንን ተከትሎም ክርስቲያኖ ሮናልዶ በ4 የተለያዩ ሊጎች ኮከብ ግብ አግቢ ሆኖ ያጠናቀቀ የመጀመሪያው ታሪካዊ ተጫዋች ለመሆን በቅቷል።

ሮናልዶ ከዚህ ቀደም በእንግሊዝ ፕሪምየር ሊግ፣ በስፔን ላሊጋ እና በጣሊያን ሴሪ ኤ ከፍተኛ ግብ አግቢ በመሆን የቻለ ሲሆን፤ አራተኛውን ደግሞ በሳዑዲ ፕሮ ሊግ አሳክቷል።

በእግር ኳሱ ዓለም የተለያዩ ክብረወሰኖች ባለቤት የሆነው ፖርቹጋላዊው ክርስቲያኖ ሮናልዶ፤ “እኔ ክብረወሰኖችን አላሳድድም ክብረወሰኖች ራሳቸው ያሳድዱኛል እንጂ” ማለቱ ይታወሳል።

ነገ በሚጀመረው የአውሮፓ ዋንጫ ላይ ከፖርቹጋል ብሄራዊ ቡድን ጋር የሚሰለፈው ክርስቲያኖ ሮናልዶ በዘንድሮው የአውሮፓ ዋንጫ ላይ 8 የተለያዩ ክብረወሰኖችን በእጁ እንደሚያስገባ ይጠበቃል።

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትስስር ይፍጠሩ

325,851FansLike
49,039FollowersFollow
13,194SubscribersSubscribe