ባለፈው ቅዳሜ በኦሮሚያ ክልል ምዕራብ ወለጋ ዞን ጊምቢ ወረዳ በግፍ ስለተገደሉ ንፁሃን ዜጎች ተጨማሪ ማብራሪያ ከመንግስት ለማግኘት የተደረገው ጥረት ሙሉ ለሙሉ አለመሳካቱን የጠቀሰው ሮይተርስ ከመንግስት ባለስልጣናት መረጃ ማግኘት አስቸጋሪ መሆኑን ዘግቧል፤
ዜና ወኪሉ በመጀመሪያ በግፍ ስለተገደሉ ዜጎች ማንንት ለማጣራት ለመንግስት ኮሚዩኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ዶ/ር ለገሰ ቱሉ ያደረገው የስልክ ጥሪ ምላሽ እንዳላገኘ የገለፀ ሲሆን የመከላከያን ምላሽ ለማካተት ለሚኒስትሩ የህዝብ ግንኙነት ሀላፊ ኮሎኔል ጌትነት ፍስሃ ያደረገው የስልክ ጥሪም ምላሽ አላስገኘም፤
ግድያው የተፈፀመበት የኦሮሚያ ክልል ኮምንኬሽን ጉዳዮች ቢሮ ሃላፊ አቶ ሀይሉ አዱኛን በስልክ ለማግኘት ጥረት ቢደረግም ስልካቸው ምላሽ አለመስጠቱን ሮይተርስ ዘግቧል፤
በመጨረሻም ሮይተርስ ሙከራ ያደረገው ለጠቅላይ ሚኒስትሩ የፕሬስ ሴክረተሪ ሀላፊ ለሆኑት ወ/ሪት ቢሌኔ ስዩም ሲሆን ስልካቸውን እንደማይነሳ እና በጭፍጨፋው ዙሪያ ላዘጋጀው ጥያቄ መልስ የሚሰጥ የኢትዮጵያ መንግስት የስራ ሀላፊ ለማግኘት አለመቻሉን ጠቅሷል።

