ሰው አንቆ የገደለው ግለሰብ በ7 ዓመት እስራት መቀጣቱ ተሰማ

ሟችን አንገቱን አንቆ በመያዝ ባደረሰበት ጉዳት ምክንያት ህይወቱ እንዲያልፍ ያደረገው ተከሳሽ በእስራት ተቀጣ፡፡

አጥናፉ እሸቴ የተባለው ግለሰብ ሰውን ለመግደል በማሰብ መስከረም 14/2016 ዓ.ም በቂርቆስ ክ/ማ ወረዳ 02 ተከሳሽ ሟች ታመነ ክፈተውን በመሳደቡ የተነሳ ጸብ ሟችን አንገቱን አንቆ በመያዝ በደረሰበት ጉዳት ምክኒያት ህይወቱ እንዲያልፍ ያደረገ በመሆኑ በፍትህ ሚኒስቴር የጠቅላይ ዐቃቢ ህግ ዘርፍ የልዩ ልዩ ወንጀል ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ዐቃቢ ህግ በፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 1ኛ ሰው ግድያና ከባድ ውንብድና ወንጀል ችሎት በፈጸመው ተራ ሰው መግደል ወንጀል ክስ አቅርቦበት ክርክር ሲደረግ ቆይቷል፡፡

በክርክሩ ሂደትም የዐቃቢ ህግ ማስረጃ ከተሟላ በኋላ ተከሳሽ እንዲከላከል ብይን ተሰጥቶ የመከላከያ ምስክሮችን በማቅረብ ያሰማ ቢሆንም የቀረበበትን ክስ ሊከላከል ባለመቻሉ ፍርድ ቤቱ በ7 ዓመት እስራት እንዲቀጣ ወስኗል፡፡

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትስስር ይፍጠሩ

325,851FansLike
49,039FollowersFollow
13,194SubscribersSubscribe