ሱዳን ከኢትዮጵያ ጋር በሚያዋስናት ድንበር ዙሪያ የተጠናከረ የጋራ የጸጥታ ጥበቃ እንደምታከናውን አስታወቀች

የሱዳን ሉዓላዊ ምክር ቤት ኃላፊ አብደል ፈታህ አል-ቡርሃን አገራቸው ከኢትዮጵያ ጋር በሚያዋስናት ድንበር ዙሪያ የተጠናከረ የጋራ የጸጥታ ጥበቃን ለማከናወን ከጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ጋር መስማማታቸውን የአገሪቱ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታወቀ።
የሱዳን ሉዓላዊ ምክር ቤት ኃላፊ አብደል ፈታህ አል-ቡርሃን የሁለት ቀናት የኢትዮጵያ ጉብኝታቸውን አጠናቀው ወደ አገራቸው መመለሳቸው ይታወቃል።
ጉብኝቱን እና የተደረጉ ውይይትችን በማስመልከት የሱዳን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ኦሜር ጋማር ኤልዲን እንደተናገሩት፤ ሁለቱ አገራት በተለይም በድንበርና በቀጠናዊ ጉዳዮች ዙሪያ ውይይት አድርገዋል። ሁለቱ ወገኖች “በድንበር፣ በልማትና በቀጠናዊ የፀጥታ ጉዳዮች ላይ በትብብር ለመስራት ስምምነት ላይ ደርሰዋል።
የአል-ቡርሀን ጉብኝት የተካሄደው የኢትዮጵያ ማዕከላዊ መንግስት ከትግራይ ክልል ጋር ችግር ውስጥ ባለበት ወቅት መሆኑን የጠቀሱት ሚኒስትሩ፤ ቀደም ሲል ሱዳን የድንበር አካባቢዎችን ለመቆጣጠር እና በግዛቷ በኩል የአማፅያን ጥቃቶችን በመከላከል ለኢትዮጵያ ስታደርግ የቆየችውን ድጋፍ አጠናክራ ትቀጥላለች ብለዋል።
የሁለቱን አገራት ታሪካዊ ግንኙነት በማጠናከር የሁለቱን ህዝቦች ፍላጎት መሰረት በማድረግ መስራት እንደሚያሰፈልግም መሪዎቹ ተስማምተዋል ብለዋል ፡፡
የድንበር ጥቃቶችን ለመከላከልና ድንበር ተሻጋሪ ወንጀሎችን ለመዋጋት ሁለቱ አገራት መስማማታቸውንም ሚኒስትሩ መግለፃቸውን ኢ.ፕ.ድ ዘግቧል፡፡

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትስስር ይፍጠሩ

325,851FansLike
49,039FollowersFollow
13,194SubscribersSubscribe