ሱዳን ውስጥ የነበሩ 177 የግብፅ የአየር ኃይል ወታደሮች ወደ ሀገራቸው እንዲመለሱ ተደረገ

ሱዳን ውስጥ የነበሩ የግብፅ ወታደሮች ወደ ሀገራቸው እንዲመለሱ ተደረገ።

የሱዳን ጦር 177 የግብፅ የአየር ኃይል ወታደሮች ወደ ግብፅ መወሰዳቸውን አስታውቋል።

የሱዳን ጦር ባወጣው መግለጫ የግብፅ ወታደሮቹ በአራት የግብፅ ወታደራዊ አውሮፕላኖች ከሰሜናዊቷ ዶንጎላ ከተማ ወደ ሀገራቸው እንዲመለሱ ተደርገዋል። ጦሩ ፤ ግብፃውያኑ ሱዳን የነበሩት የጋራ የአየር ሃይል ልምምድ ለማድረግ እንደነበር አመልክቷል።

የግብፅ ጦር የሰራዊት አባላቱ ሱዳንን ለቀው ስለመውጣታቸውን እስካሁን በይፋ ባያሳውቅም ሱዳን ያሉ ወታደሮቹን ወደ ሀገራቸው እንዲመለሱ ለማድረግ ከሱዳን ባለስልጣናት ጋር በመስራት ላይ እንደሚገኝ ገልጾ ነበር።

የሱዳን ጦር አሁን መመለሳቸውን የገለፃቸው የግብፅ ወታደሮች ከቀናት በፊት በRSF የተያዙትን እንዳልሆነና በRSF ስር ያሉት 28 ወታደሮች መሆናቸውንና አሁንም በነሱ እጅ እንደሚገኙ ገልጿል።

ትላንት ምሽት ግን የሱዳን ጦር ወደ ግብፅ የተወሰዱት በRSF የተያዙት / የታሰሩ ወታደሮች መሆናቸውን ገልጾ መግለጫ አውጥቶ ነበር ፤ ይህንን መግለጫም ዋቢ በማድረግ ዓለም አቀፍ መገናኛ ብዙሃን ዘገባዎችን ሰርተው ነበር።

ጦሩ ዛሬ ባወጣው መግለጫ የትላንቱ መግለጫው ትክክለኛ እንዳልሆነ አመልክታል። የተያዙት / የታሰሩት በሚል የገባው ቃል ሳይታወቅ በስህተት ነው ብሏል።

አሁን ወደ ግብፅ እንዲመለሱ የተደረጉት ወታደሮች ግጭቱ በተቀሰቀሰበት ወቅት ማራዊ ውስጥ የነበሩ ነገር ግን ከኤርፖርት ውጭ ስለነበሩ በRSF ያልተያዙ ናቸው ሲል አስረድቷል።

የሱዳን ውጊያ በተጀመረበት ወቅት በጄነራል መሐመድ ሃምዳን ደጋሎ (ሄሜቲ) የሚመራው የሱዳን ፈጥኖ ደራሻ (RSF) ሜሮዌ ላይ የግብፅ ወታደሮችን #መማረኩን ማሳወቁ ይታወሳል።

ከቀናት በፊት የግብፁ ፕሬዜዳንት አብድል ፈታህ አል ሲሲ ሱዳን ውስጥ የተያዙት የግብጽ ወታደሮች፣ በዚያ የተገኙት ከሱዳን አቻዎቻቸው ጋራ ወታደራዊ ልምምድ ለማድረግ እንጂ ፤ የትኛውንም ወገን ለመደገፍ አለመኾኑን ገልጸዋል።

ይህንን የገለፁት ከግብጽ ከፍተኛ ወታደራዊ ም/ቤት ጋር ስብሰባ በተቀመጡበት ወቅት ሲሆን የወታደሮቹን ደህንነት በተመለከተ ከRSF ጋር እየተነጋገሩ መሆኑን አስታውቀዋል።

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትስስር ይፍጠሩ

325,851FansLike
49,039FollowersFollow
13,194SubscribersSubscribe