ሱዳን የተመድ የጸጥታው ም/ቤት በግድቡ ጉዳይ እንዲሰበሰብ ጠየቀች

የዓረብ ሊግ ኢትዮጵያ የማትስማማ ከሆነ ሱዳን እና ግብፅ ለጸጥታው ም/ቤት ረቂቅ የውሳኔ ሀሳብ እያዘጋጁ ነው ብለዋል፡፡

ኢትዮጵያ ከአፍሪካ ህብረት ውጭ አደራዳሪዎችን ለማሳተፍ ፈቃደኛ እንዳልሆነች በተደጋጋሚ ስትገልጽ ቆይታለች፡፡

አትዮጵያ በጉባ ሸለቆ እየገነባችው ባለ “የታላቁ ህዳሴ ግብድ ፕሮጀክት”ና ተያያዥ ጉዳዮችን በተመለከተ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት(ተመድ) የፀጥታው ም/ቤት እንዲሰበሰብ ስትል ሱዳን ጠየቀች፡፡

የሱዳን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ማሪያም ሳዲቅ አል-ማህዲ የተመድ የጸጥታ ምክር ቤት ግድቡ “በሚሊዮኖች በሚቆጠሩ ሰዎች ደህንነት ላይ የሚያሳድረው ተጽዕኖ” ለመወያየት በተቻለ ፍጥነት ስብሰባ እንዲያካሂድ ጥሪ ማቅረባቸው ሮይተርስ ዘግቧል፡፡

ሚኒስትሯ ለምክር ቤቱ ሃላፊ በፃፉት ደብዳቤ “ያለውን አለመግባባት የሚያባብሰው እና ለአህጉራዊም ሆነ ለዓለም አቀፋዊ ሰላምና ደህንነት ስጋት የሆነው ግድብ“ እንዲሁም ”በተናጠል የሚሞላውን ግድብ” እንዲቆም የጸጥታው ም/ቤት ኢትዮጵያን እንዲያሳስብ ሲሉ ጥሪ አቅርበዋል፡፡

በሱዳን በኩል እንዲህ ቢባልም ግን በዚህ ጉዳይ ላይ በኢትዮጵያ መንግስት በኩል እስካሁን የተባለ ነገር የለም፡፡

በአፍሪካ ህብረት የተደገፈው ድርድር አጥጋቢ ሳይሆን መቅረቱን ተከትሎ ሱዳንና ግብፅ በሁሉም ደረጃዎች በጋራ ለመስራትና በድረድር ሂደቱ ኢትዮጵያ ላይ ጫና ለመፍጠር ባለፈው ወር መስማማታቸው የሚታወስ ነው፡፡ የዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ጣልቃ እንዲገባ ጥሪ ማቅረባቸውንም ጭምር፡፡

የዓረብ ሊግም ቢሆን የተመድ የጸጥታው ም/ቤት ኢትዮጵያ ሁለተኛው የሙሌት ተግባርን ከማከናወኗ በፊት ሀገራቱ ባላቸው ልዩነት እንዲመክር ከወር በፊት ጥሪ አቅርቦ ነበር፡፡ ምንም እንኳን ኢትዮጵያ በውጭ ጉዳይ መስርያ ቤቷ በኩል በሰጠችው ምላሽ የዓረብ ሊግን መግለጫ ሙሉ በሙሉ እንደማትቀበለው በወቅቱ ብትገልጽም፡፡

በተመድ የዓረብ ሊግ ተወካይ ማጌድ አብደል ፋታህ ኢትዮጵያ የማትስማማ ከሆነ ሱዳን እና ግብፅ ለጸጥታው ም/ቤት ረቂቅ የውሳኔ ሀሳብ እያዘጋጁ መሆኑን በትላንትናው ዕለት ተናግረዋል፡፡

የሊጉ ተወካይ ማጌድ አብደል የዓረብ ሊግ ሀገራት ረቂቁ እንዲፀድቅ ጫና እንደሚያደርጉና ይህንን የሚቀለብሱ የዓለም ኃያላን ይኖራሉ ብለው እንደማይጠብቁም ነው ሳዳ ኤልባላድ ለተባለ የግብፅ የግል የቴሌቪዥን ጣቢያ የተናገሩት፡፡

ኢትዮጵያ ከዚህ በፊት ከአፍሪካ ህብረት ውጭ አደራዳሪዎችን ለማሳተፍ ግብፅ እና ሱዳን ያቀረቡትን ጥሪ ውድቅ ማድረጓ ይተዋሳል፡፡

ኢትዮጵያ የኢኮኖሚ ልማት እና የኃይል ማመንጨት ተስፋዋን በታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ እውን እንደሚሆን በማመን ለፕሮጀክቱ መሳካት ሌት ተቀን እየታተረች ቢሆኑም፤ ሁለቱ የተፋሰስ ሀገራት – ግብፅ እና ሱዳን – በግድቡ ሙሌትና ስራዎች ላይ አስገዳጅ ስምምነት ካልተፈረመ በማለት እጅጉን የተጨነቁ ይመስላሉ፡፡

ግብፅ በአባይ ወንዝ ላይ እስከ 90% የሚሆነውን ንፁህ ውሃ የተመሮኮዘች ሀገር እንደመሆኗ ግድቡን እንደ ስጋት ሰትመለከተው ሱዳን በበኩሏ የናይል ግድቦች እና የውሃ ማሰራጫ ጣቢያዎች ጉዳይ ያሳስባታል፡፡

Kumneger Media
Kumneger Media
Kumneger Media is a News and Entertainment Website & Channel. Kumneger Media in addition to News and Entertainment it is the hub of Politics, Movies, Drama, Music, Comedy, Documentary and More!

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትስስር ይፍጠሩ

325,851FansLike
49,039FollowersFollow
13,194SubscribersSubscribe