የሲኖትራክ ተሽከርካሪ ያለበትን የጥራት እና የቴክኒክ ችግር እስኪያሻሽል ድረስ ወደ ሀገር ውስጥ እንዳይገባ መታገዱን የጉምሩክ ኮሚሽን አስታውቋል።
የጥራት ጉድለቱ በየጊዜው የሰው ሕይወት ብሎም ንብረት እንዲጠፋ ምክንያት በመሆኑ፤ አምራች ድርጅቱ ማሻሻያ እስከሚያደርግ ድረስ ተሸከርካሪው ወደ ሀገር ውስጥ እንዳይገባ መከልከሉን የኮሚሽኑ የኮሙኒኬሽን ዳይሬክተር ዘሪሁን አሰፋ ለኢቢሲ ገልጸዋል።
ክልከላው ከግንቦት 27 ቀን 2017 ዓ.ም ጀምሮ ተግባራዊ መደረጉን ገልጸዋል። በዚህም ከተጠቀሰው ዕለት ጀምሮ ምንም ዓይነት የማስገቢያ ፈቃድ እንዳልተሰጠ አረጋግጠዋል።

