ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ በጤና እና ደህንነት አጠባበቅ ላይ ባሳየው ብቃት ቮዳኮም ግሩፕ አገልግሎት ከሚያቀርብባቸው አገራት የቀዳሚነት እውቅናን አገኘ።
በካይሮበተካሄደው የቮዳኮም ቡድን የ2025 አመታዊ የጤና ደህንነት እና የአገልግሎት አቅራቢዎች መድረክ ላይ ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ የአመቱ ምርጥ ተብለን እውቅናን አግኝተል።
ሽልማቱ በቮዳፎን ግሎባል የጤናና ደህንነት ኃላፊ የተበረከተ ሲሆን በስነስርዓቱም ድርጅቱ ለጤናና ደህንነት ያለውን የማያወላውል ቁርጠኝነት አድንቀው በዚህ ረገድ በሁሉም የቮዳኮም ገበያዎች ላይ ያደረግነውን የላቀ ተፅእኖም አስታውሰዋል።
ጤና እና ደህንነት የአንድ ጊዜ ውጤት ሳይሆን በስትራቴጂ የተደገፈ የተከታታይ ቁርጠኝነት ውጤት ነው። <በዚህም የጤናና ደህንነት የስራ ክፍላችንን ጨምሮ ሁሉም ሰራተኞች ላበረከቱት አስተዋጻኦ እናመሰግናለን።> ብላል ሳፋሪኮም፡፡
ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ በጤና እና ደህንነት አጠባበቅ ላይ ባሳየው ብቃት የቀዳሚነት እውቅናን አገኘ

