ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ : “ተረክ በጉርሻ” የተሰኘ ሽልማት ለደንበኞቹ ማዘጋጀቱን አስታወቀ

 ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ “ተረክ በጉርሻ” የተሰኘ የሽልማት እጣ ለደንበኞቹ ማዘጋጀቱን አስታወቀ
በኢትዮጵያ የቴሌኮም አገልግሎት መስጠት ከጀመረ ጥቂት ወራትን ያስቆጠረው ሳፍሪኮም ነባርና አዳዲስ ደንበኞቹን ተጠቃሚ የሚያደርግ የሽልማት እጣ ማሰናዳቱን ገልጿል።
በሽልማቱ ለመሳተፍ ለአዳዲስ ደንበኞች 3 የዕጣ ቁጥሮችን ለማግኘት የሳፍሪኮም ሲም ካርድ በመግዛት በ24 ሰዓት ውስጥ ካርድ መሙላት ይጠበቃል ተብሏል።
አንድ የዕጣ ኮድ ለማግኘት ደግሞ የአየር ሰዓት መሙላት ወይም የድምፅና የአጭር መልዕክት ጥቅል መግዛት በቂ መሆኑ ተነግሯል፡፡
የዕጣ መርሐ ግብሩ በየዕለቱ፣ በየሁለት ሳምንቱ እና በየወሩ የሚካሄድ ሲሆን ከመጋቢት 27 እስከ ሰኔ 27 ቀን 2015 ዓ.ም ይቆያል።
አሸናፊ ለሚሆኑ እድለኞች 3 ዘመናዊ የቤት መኪኖች፣ 7 ባለ ሦስት እግር ባጃጆች እና 7 ሞተር ሳይክሎች በሽልማት መልክ የተዘጋጁ ሲሆን በየዕለቱ የአየር ሰዓት ስጦታዎች እንደሚኖሩም ከተቋሙ ኋላፊዎች ሰምተናል፡፡
የሳፍሪኮም ዋና ስራ አስፈፃሚ አንዋር ሶሳ ባስተላለፉት መልዕክት የሽልማት ዕጣው ዓላማ የተቋሙን ምርትና አገልግሎት ደንበኞቹን ተጠቃሚ በማድረግ ማስተዋወቅ ነው ብለዋል።
ሳፍሪኮም በአሁኑ ወቅት በመላ ሀገሪቱ ያሉት የደንበኞች ቁጥር 2 ነጥብ 8 ሚሊዮን መድረሱን ተናግሯል።

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትስስር ይፍጠሩ

325,851FansLike
49,039FollowersFollow
13,194SubscribersSubscribe