ስለ የማህፀን በር ካንሰር ይህን ያዉቁ ኖሯል?

በአለማችን ያሉ ሴቶችን በብዛት ከሚያጠቁ የካንሰር በሽታዎች አራተኛውን ደረጃ የያዘው የማህፀን ጫፍ
ካንሰር የሚባለው የካንሰር ዓይነት ነው፡፡
እንደ ማንኛዉም ካንሰር ህዋሶች ከተለመደው ወጣ ባለ ወይም ጤናማ ባልሆነ መልኩ ሲያድጉ ብሎም ሲባዙ ይፈጠራል ።
የማህጸን በር ካንሰር በጊዜ ህክምና ካላገኘ በማህጸን አካባቢ ያሉ የሰውነት ክፍሎችን ሊወር፣ ወደሌላ የሰውነት ክፍሎቻችንም ሊሰራጭ ይችላል።

ይህን ለመከላከል ምን እናድርግ ?
-ቅድሚያ በሚሰጡ ክትባቶችን በሰኣቱ መዉሰድ
-በጊዜ ህመሙን አግኝቶ ለማከም የሚረዳውን የማህፀን ጫፍ ካንሰር ምርመራ (papsmear) ማድረግ

ይህን የማህፀን ጫፍ ካንሰር ምርመራ ማን ያድርግ?
ማንኛዋም ሴት እድሜዋ 21 አመት ከሆነበት ወይም ግንኙነት ከጀመረችበት ከ3 አመት ጀምሮ በየ3 አመቱ ምርመራ እንድታደርግ ይመከራል።

ለማህፀን በር ጫፍ ካንሰር ምን ያጋልጠናል?
1, (HPV) ቫይረስ
ከ99% በላይ የሚሆነው የማህፀን በር ካንሰር ከዚህ ቫይረስ ጋር በተያያዘ የሚመጣ ነው።
ሂዩመን ፓፒሎማ ቫይረስ በግብረ ስጋ ግንኙነት ጊዜ የሚተላለፍ ቫይረስ ሲሆን ብዙውን ጊዜ በሽታው ምልክቶች ሳይኖሩት በሰውነት ውስጥ ኖሮ የማህፀን ጫፍ ካንሰር ሊያመጣ ይችላል፡፡
2, ሲጋራማጨስ
3, የአባላዘር በሽታ የተያዙ ሴቶች (HIV) ጨምሮ
4, ከ5 አመት በላይ የወሊድ መቆጣጠሪያ እንክብል መዉሰድ ይጠቀሳሉ፡፡

ምን ምን ምልክቶች ሊኖሩን ይችላሉ?
በአብዛኛው የማህፀን ጫፍ ካንሰር ወደ ውስጠኛው የማህፀን በር ክፍል ገብቶ በደንብ ከመዛመቱ በፊት በተያዘችው ሴት ላይ ምንም ዓይነት ምልክቶች አያሳይም፡፡
የማህፀን ጫፍ ምርመራ (papsmear) ተሰርቶ ከመዛመቱ በፊት ማወቅ ከተቻለ ግን ከነጭራሹ ማጥፋት ይችላል፡፡

ነገር ግን የሚከተሉት ምልክቶችን ሊኖሩ ይችላሉ:-
– ከወር አበባ ውጪ ከማህፀን የደም መፍሰስ
– በግንኙነት ጊዜ ህመም ወይም መድማት መኖር
– ሀይለኛ ሽታ ያለው የማህፀን ፈሳሽ መኖር
– እንዲሁም የማህፀን አካባቢ ህመም እንደ ምልክት ሊታይ ይችላል፡፡

*ከላይ የተጠቀሱት ስሜቶች ካልዎት ወይንም የማህፀን በር ካንሰር ምርመራም ኣገልግሎት ማግኘት ከፈለጉ ቡልቡላ በሚገኘዉ ማእከላችን በመምጣት የማህፀን እና ፅንስ ስፔሻሊስታችንን በማንኛዉም የስራ ሰኣት ማግኘት ይችላሉ፡፡

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትስስር ይፍጠሩ

325,851FansLike
49,039FollowersFollow
13,194SubscribersSubscribe