ስቶክ ማርኬትና ስቶክ ኤክስቼንጅ

ሴኪውሪቲስ ምን ማለት ነው?
ሴኪውሪቲስ ለሚለው ቃል ተዛማጅ ፍቺ ነው ብዬ የማስበው የንዋይ ሰነድ የሚለውን ነው፡፡ ንዋይ ገንዘብ ማለት ሲሆን ሰነድ ደግሞ በሕግ የተደገፈ ውል ነው፡፡ ሴኪውሪቲስ ኤክቼንጅ ማለት ደግሞ እነዚህ የንዋይ ሰነዶች የሚገዙበትና የሚሸጡበት ገበያ ነው፡፡ ዋጋ ያላቸው የገንዘብ ሰነዶች ብሎ መተርጎምም ይቻላል፡፡ የበለጠ አራቆ ለመተንተን ፤ ሴኪውሪቲስ ማለት የሕግ ድጋፍ ያላቸው፣ ወረቀት ላይ ያሉ ሀብታት ፣ ወይም በገንዘብ የሚመነዘሩ ሰነዶች ብሎ መተርጎም ይቻላል፡፡ባጭሩ ግን የንዋይ ሰነድ ማለት ነው፡፡
Types of securities
የሰነድ መዋዕለ ንዋይ ገበያ ላይ የሚሸጡትና የሚለወጡት ሰነዶችን ዘርዝሮ ማየቱ ጠቃሚ ነው፡፡
ሴኪውሪቲስ ወይም የንዋይ ሰነዶች ብዙ ቢሆኑም በሶስት ከፍሎ ማየት ይቻላል፡፡ ቢያንስ ከስቶክ ማርኬት ( የአክስዮን ገበያ) ጋር በተዛመደ መልኩ፡፡
Equity securities ( የራስ ሀብት/ የወረት ሰነዶች) ለግዜው ስቶክ ማርኬት ለ ኤኩቲ ሴኪውሪቲ ጥሩ ምሳሌ ነው፡፡
Debt securities ( የብድር/ እዳ ሰነዶች ) ለዚህ ደግሞ ቦንድ ጥሩ ምሳሌ ነው፡፡
Securities Market ( የነዋይ ሰነድ ገበያ)
ስቶክም ( አክስዮን) ቦንድም( የ ዕዳ ሰነድ) የራሳቸው ሰፊ ትንታኔ ስላላቸው ወደፊት እናየዋለን፡፤ ግን ባጠቃላይ ሴኪውሪቲስ ማርኬት ማለት እነዚህ የገንዘብ ሰነዶች ( stok , bond etc) የሚሸጡበትና የሚገዙበት የልውውጥ ቦታ ነው፤
ማርኬትና ኤክስቼንጅ መሀል ያለ የትርጉም ልዩነት
የስቶክ ማርኬትንና ስቶክ ኤክስቼንጅን እያምታቱ መጠቀም ልማድ ሆኗል፡፡ ገበያው ላይ ደምቆ ሚታየው ስቶክ ወይም የአክስዮን ገበያ ስለሆነ ፣ ስቶክ ማርኬትን ና ስቶክ ኤክስቼንጅን አደባልቆ ማውራቱ የተለመደ ስሀተት ሆኗል፡፡
ስቶክ ማርኬት ስንል ዘርፈ ሰፊ ነው፡፡ ቢያንስ አምስት አካላትን የያዘ ትልቅ ጽንሰ ሀሳብ ነው፡፡ የአክስዮን ገበያ ወይም ስቶክ ማርኬት ኢንቨስተሮችን ፣ ሻጮችን፣ ደላሎችን ፣ ሕግ አውጭና አስከባሪ የመንግስት አካላትን እና ስቶክ ኤክስቼንጆችን የያዘ ነው፡፡ ስለዚህ አንድ ሰው ስቶክ ማርኬት ወይም የአክስዮን ገብያ ሲል፣ እየጠቀሰ ያለው ትልቅ ጽንሰ ሀሳብን ነው፡፡
ሴሪውሪቲስ ማርኬት ስንል ደግሞ እነዚን አምስቱን አካላት የያዘ የብዙ ሰነዶች ( ስቶክ እና ቦንድ ብቻ ያይደለ) ትልቅ ጽንሰ ሀሳብ ይሆናል ማለት ነው፡፡
በተዋረድ ስናስቀምጠው፣ ሴሪውሪቲስ ማርኬት ወይም የየንዋይ ሰነድ ገበያ ሰፊ ነው፡፡ ብዙ ሴኪውሪቲዎችን ( የኢኪውቲ እና ዴት ) የሚገበያዩበት ትልቅ ገበያ ነው፡፡ ብዙ አካላትን በተለይ ከላይ የተጠቀሱትን አምስት አካላት ይይዛል፡፡
ስቶክ ማርኬት ስንለው፣ ወደ አክስዮን ገበያ እናጠበዋለን፡፡ በብዛት የሚያመለክተው የኢኪውቴ ሴሪውሪቲስን ይሆናል፡፡ ስለዚህ ስቶክ ማርኬት ከ ሴኪውሪቴስ ማርኬት ያንሳል፡፡
ስቶክ ኤክስቼንጅ ስንል ደግሞ፣ የበለጠ እያጠበብነው እንሄዳለን፡፡ ስቶክ ኤክስቼንጅ ፣ የገንዘብ ሰነዶች የሚሸጡበት ተቋም ማለት ነው፡፡ ይሄም ማለት ፣ ገ ዥና ሻጭ ተገናኝተው የሚገበያዩበት ቨርችዋል ወይም ፊዚካል የመገናኛና መገበያያ ቦታ ነው፡፡
በተዋረድ ስናስቀምጠው
ሴኪውሪቲስ ማርኬት ትልቅ ነው፡፡ ስቶክ ማርኬት ደግሞ የሴኪውሪቲስ ማርኬት አንዱ ንኡስ አካል ነው፡፡ ስቶክ ኤክስቼንጅ ደግሞ የስቶክ ማርኬት አንዱ ንኡስ አካል ነው፡፡
ልዩነቱን በ ነጥብ ስናየው
ስቶክ ማርኬት ስቶክ ኤክስቼንጅ ሥርዓት ነው፡፡ ትልቅ ጽንሰ ሀሳብ ነው የመገበያያ ቦታ ነው;ቢያንስ አምስት አካላትን ይይዛል አንድ ገብያ ላይ ብቻ ያተኮረ ነው’አላማውም ሙሉ የሰነድ ግብይትን ማሳለጥ ነው ለአክስዪን ግብይት ቦታን መፍጠር ነው;ምሳሌ የኢትዮጵያ አክስዩን ገበያ መርካቶ ስቶክ መለዋወጫ US Stock Market New York Stock Exchange
የቃላት ፍቺ
ስቶክ ፡ አክስዮን
ስቶክ ማርኬት ፡ የአክስዮን ገበያ
ስቶክ ኤክስቼንጅ ፡ አክስዮን መገበያያ ቦታ ( ፊዚካል ወይም ቨርችዋል)
ሴኪውሪቲስ ፡ የንዋይ ሰነድ
ሴኪውሪቲስ ማርኬት ፡ የንዋይ ሰነዶች ገበያ
ቦንድ ፡ የዕዳ ሰነድ
ስቶክ ግን ምንድነው? ለምንስ ይሸጣል ለምንስ እንገዛለን?
*****
ስቶክ ምንድነው?
Stock በደረቁ ስንተረጉመው አክስዮን ማለት ነው፡፡ አክስዮን የሚለው ቃል ከፈረንሳይኛ የተወሰደ አሁን ግን አማርኛ የሆነ ቃል ነው፡፡ በይበልጥ ስቶክን ሊገልጸው የሚችለው ቃል ድርሻ ነው፡፡ ስቶክንም የገዛ ሰው ባለ አክስዮን ወይም ባለ ድርሻ ማለት ይሆናል፡፡ ይሄ በደምሳሳ ትርጉሙ ነው፡፡
ጠለቅ ያለ ትርጉሙ ደግሞ ፣ የአንድ ድርጅት ድርሻ ወይም ስንጥቅጣቂ ማለት ነው፡፤
አንድ ሰው ስቶክ ( ድርሻ/ አክስዮን ) ገዛሁ ሲል የአንድድ ድርጅትን ድርሻ ፣ የድርጅትን ባለቤትነት ድርሻ ገዛሁ ማለቱ ነው፡፡ ስቶክ ባጭሩ የአንድ ድርጅት ባለቤትነት ወይም ድርሻን የሚያረጋግጥ ሰነድ ነው፡፡
አንዳንድ የኤኮኖሚ ባለሙያዎች Equity ( የራስ ሀብት) የሚለውን ጽንሰ ሀሳብ ስቶክ በማለት እያዛነቁ ይጽፋሉ፡፡ ትንሽ ማብራርያ ቢፈልግም ወደፊት ስለምናየው ላሁኑ እንቀጥል፡፡
ባጭሩ Stock, Share, Equity ከሞላ ጎደል አንድ ጽንሰ ሀሳብን የሚያሳዩ ቃላቶች ናቸው፡፡ Share holder , stock holder እና መሰል ስሞችም የሚያመላክቱት የአክስዮን ባለቤትነትን ነው፡፡ ባጭሩ የኩባንያ ባለቤትነትን የሚያመለክቱ ናቸው፡፡ በገዛነው ድርሻ ልክ፡፡
ወደ ሳይንሳዊው ትርጉም ስንመጣ ስቶክ
ሴኪውሪቲ ( ዋጋ ያለው ሰነድ ወይንም የንዋይ ሰነድ ነው)
በገዛነው አክስዮን ልክ የድርጅት ባለቤትነትን የሚያረጋግጥ ሰነድ ነው
ስቶክ ማርኬት
************
ይህንንም የባለድርሻ ሰነድ የምንገዛበትና የምንሸጥበት ቦታ ስቶክ ማርኬት ወይም የአክስዮን ገበያ በመባል ይታወቃል፡፡ የተለያዩ ድርጅቶች ድርሻ የሚገዛበትና የሚሸጥበት፣ የድርጅቶች ድርሻ ለገበያ የሚወጣበት፣ የሚሸጥበት ፣ የሚለወጥበት ፣ ገዥ ኢንቨስተሮችና ሻጭ ድርጅቶች አክስዮንን ወይም ድርሻን የሚገበያዩበት ቦታ የአክስዮን ገበያ ወይም ስቶክ ማርኬት በመባል ይታወቃል፡፡
ለምሳሌ አንድ ሰው መርካቶ ይሄዳል፡፡ ከመርካቶም አትክልት ተራ ( አሁን ቢቀየርም ) ሄዶ አንድ ፍራፍሬ ገዝቶ ይመጣል፡፡ መርካቶን እንደ ሴኪውሪቲስ ማርኬት መውሰድ እንችላለን፡፡ ምክንያቱም መርካቶ ውስጥ የሚሸጠው ዕቃ ብዙ ነው፡፡ በዛ ላይ መርካቶ ውስጥ ደላሎች አሉ፣ ሕግ አስከባሪዎች አሉ፣ ገዥዎች አሉ፣ ሻጮች አሉ፡፡ ስለዚህ መርካቶ የገበያ ሥርዓት ነው፡፡ ገበያ ማለት ሻጭንና ገዥን ብቻ ሳይሆን ብዙ አካላትን የያዘ ስለሆነ፡፡
ሴኪውሪቲስ ማርኬት ብዙ የገንዘብ ሰነዶች የሚሸጡበት ትልቅ ሥርዓት ነው፡፡ ልክ እንደ መርካቶ፡፡ ሕግ የሚያወጡና የሚያስከብሩ የመንግስት አካላት፣ ብሮከርስ( ደላሎች)፣ ማርኬት ሜከርስ፣ ገዥዎች፣ ሻጮች ወዘተ አሉበት፡፡ አትክልት ተራ ግን አንድ አይነት ነገር የሚሸጥበት የገበያው አንድ ንኡስ አካል ነው፡፡ ስቶክ ማርኬትም፣ ከብዙ ሴኪውሪቲዎች ውስጥ ስቶክና መሰል የነዋይ ሰነዶች የሚሸጡበትና የሚለወጡበት ቦታ ነው፡፡
አትክልት በያይነቱ ተዘርግቶ የሚሸጥበት ቦታ አትክልት ገበያ እንደሚባለው ሁሉ፣ የተለያዩ ኩባንያዎች ድርሻ በያይነቱ የሚሸጥበት ገበያ ደግሞ የአክስዮን ገበያ ይባላል፡፡ በግ ለመግዛት በግ ተራ እንሂድ እንደሚባል፣ ከብት ለመግዛት ሰንጋ ተራ እንሂድ እንደሚባል፣ ድርጅት/ ኩባንያ ድርሻ ለመግዛት የሚኬድበት ገበያ የስቶክ ማርኬት ወይም አክስዮን ገበያ ይባላል፡፡
ለምሳሌ
ዮሐንስ ዳቦ ቤት ለሽያጭ ቀረበ እንበል፡፡ በግ ተራ ሄዶ አይሸጠውም፡፡ ድሮ ድሮ ይሄን ስራ አልፎ አልፎ ባንኮች ሲሰሩት እናይ ነበር ( ኢትዮጵያ ውስጥ) ፡፡ አሁን ግን ኢትዮጵያም ቢሆን ፣ የድርጅት ድርሻ መግዛት የፈለገ ሰው የሚሂደው ስቶክ ማርኪት ይሆናል ማለት ነው፡፡
ወደ ምሳሊአችን እንመለስና ፣ የዮሓንስ ዳቦ ቤት ፣ የአንዱ አክስዮን ዋጋ አንድ ሺህ ነው እንበል፡፡ የቀረበውም አክስዮን ብዛት 100 ነው እንበል፡፡ አንድ ሰው አስር ሺህ ብር አውጥቶ 10 አክስዮኖችን ገዛ፡፡ ይህ ሰው የዮሓንስ ዳቦ ቤት 10% ባለቤት ሆነ ማለት ነው፡፡
ስለዚህ ድርጅቱ ከሚያገኘው ትርፍ አስር ፐርሰንት የመካፈል መብት አለው፡፡ በባለቤትነትም አኳያ ፣ የድርጅቱ 10% ባለቤት ነው፡፡ ባለቤት ሲባል ግን በቀን ተቀን ሥራ ውስጥ ገብቶ ይሳተፋል ማለት ላይሆን ይችላል፡፡ ስራውን በባለሙያዎች ይሰራል፣ ግን የድርጅቱ አስር ፐርሰንት ባለቤት አክስዮኑን የገዛው ሰው ነው፡፡
ወደ እውኑ ዓለም ስንሄድ ፣ የፌስ ቡክ መስራች ማርክ 347 ሚሊዮን የፌስ ቡክ አክስዮኖች ባለቤት ነው( አሁን ባለው ሁኔታ) ፡፡ ይሄ ደግሞ የድርጅቱ 13.5% ( አስራ ሶስት ነጥብ አምስት ፐርሰንት ባለቤት ያደርገዋል፡፡ ትልቁ ሚስጥር እዚህ ላይ ነው ያለው፡፡
ፌስ ቡክ ትንሽዮ ፕሮጀክት ነበረች፡፡ እነ ማርክ ግን በሃርቫርድ ዩንቨርስቲ ካምፓስ ተማሪዎች ለማገናኘት በሚል እቅድ የጀመሩትን ትንሽዪ ፕሮጀክትን ፣ ለምን ዓለምን የሚያገናኝ ትልቅ ፕሮጀክት አናደርገውም ብለው ለማስፋት አቀዱ፡፡ ትንሷን ፕሮጀክት ትልቅና ግሎባል ለማድረግ ግን ብዙ ገንዘብ ያስፈልጋቸዋል፡፡
ስለዚህ ሁለት አማራጮች አላቸው፡፡ አንደኛው በራሳቸው ገንዘብ ማስፋፋት ነው፡፡ ሁለተኛው ደግሞ ገንዘብ ተበድሮ ማስፋፋት ነው፡፡ እነሱ ግን የድርጅቱን አስዮን ለገበያ አቅርበው ለመሸጥና ከዛም ያገኙትን ገንዘብ ተጠቅመው ፌስ ቡክን ማስፋፋት በሚለው ሀሳብ ጸንተው ፌስ ቡክን ለገበያ አቀረቡት፡፡
በአጭሩ
*********
ድርጅቶች ፣ ቢዝነሳቸውን ለማሳደግ ገንዘብ ሲፈልጉ ድርጅታቸው በአክስዮን ከፋፍለው ይሸጣሉ፡፡ ከዛ ባገኙት ገንዘብም ድርጅታቸውን ያስፋፋሉ፡፡
ኢንቨስተሮች ( ወይም የድርጅት አክስዮንን የሚገዙ ሰዎች / ድርጅቶች) ፣ ድርሻን የሚገዙት ደግሞ ፣ ዛሬ የገዙት ድርሻ ወይም አክስዮን ከጥቂት ግዜያት በኋላ የዋጋ ዕድገት መጨመር ስለሚያሳይ ና ድርጅቱ ሲታረፍም የትርፍ ክፍፍል ድርሻ ስለሚኖራቸው ነው፡፡
Stock / Share አክስዮን ፣ ድርሻ
Stock holder ፣ ባለድርሻ፣ የድርጅት ስንጥቅጣቂ ባለቤት ፣ ባለ አክስዮን
Stock Market የአክስዮን / የባለድርሻ ገበያ
Equity ፣ የራስ ሀብት
Capital gain የዋጋ መጨመር/ ዕድገት
Dividend ትርፍ ክፍፍል.
Credit: Addis Perspective

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትስስር ይፍጠሩ

325,851FansLike
49,039FollowersFollow
13,194SubscribersSubscribe