ስንሞት በሕይወት ታሪካችን ላይ እንዲጻፍ እና እንዲነበብልን የምንፈልገው ነገር ምንድን ነው?

አልፍሬድ ኖቤል
በ1888 አንድ ታዋቂ የፈረንሳይ ጋዜጣ በአንድ እትሙ ይዟቸው ከወጣቸው ዜናዎች መካከል አንዱ የተሳሳተ ነበር ።ጋዜጣው ይዞት የወጣው የዜና እረፍት ሀተታው ርዕስ ‘የሞት ነጋዴው አረፈ ‘ይላል ።የዜና ዕረፍት ሀተታው ሲቀጥል እንዲህ ይላል ።” በሰው ልጅ ታሪክ ውስጥ ታይቶ በማይታወቅ መልኩ ብዙ ሰዎችን በአንዴ የሚፈጅ ፈጠራ በመፈልሰፍ ሀብታም ለመሆን የበቃው ዶክተር አልፍሬድ ኖቤል ትላንትና አረፈ ።”በእርግጥ ዜና ዕረፍቱ የተሳሳተ ነበር ።የሞተው የዳይናሚት ፈልሳፊው ኖርዌያዊው አልፍሬድ ኖቤል ሳይሆን ወንድሙ ነበር ። ምናልባትም ጋዜጣው በቀጣዩ እትም ስለተፈጠረው ስህተት ይቅርታ ጠይቆ ስህተቱን አርሞ ሊሆን ይችላል ።ይሁን እንጂ ይህ በስህተት የታተመ የዜና እረፍት በዳይናሚት ፈጣሪው በዶክተር አልፍሬድ ኖቤል ስነልቦና ላይ ያሳደረዉ ተጽዕኖ የዋዛ አልነበረም ።
አልፍሬድ ኖቤል በዚህ ዜና ዕረፍት ሳቢያ ወደፊትከሞተ በኋላ ዐለም እንዴት እንደሚያስተውሰው ወለል ብሎ ታየው ።አዎን በርግጥም የዳይናሚት ፈልሳፊ ነው ፤ ከዚያ በፊት ታይቶ በማይታወቅ መልኩ ባንዴ በርካቶችን የሚፈጅ የዕልቂት መሣሪያ ፈጣሪ ነው ።በዚህ ፈጠራው ሳቢያም የናጠጠ ሀብታም ለመሆን በቅቷል ።ታዲያ ከሞት ነጋዴነት ውጭ ዐለም በምን ሊያስታውሰው ኖሯል ።አልፍሬድ ኖቤል አንድ ነገር ማድረግ እንዳለበት ተሰማው ።እናም ከመሞቱ አንድ አመት አስቀድሞ በሕዳር 18 1895 ካለው ጠቅላላ ሀብት 94 % ያህሉን በስሙ ለሚቋቋመው የኖቤል ሽልማት ሸላሚ ድርጅት ኖቤል ፋውንዴሽን ማቋቋሚያና ለሽልማቱ ማበርከቱን የሚገልፀው የኑዛዜው ሰነድ ላይ ፈረመ ።…. በኖቤል ኑዛዜ መሠረት የኖቤል ሽልማት በአምስት ዘርፎች በመሠጠት የጀመረ ሲሆን (በፊዚክስ ፣በኬምስትሪ ፣በሕክምና ፣በስነጽሁፍና በሰላም) ከ1969 ወዲህ ደግሞ ኢኮኖሚክስ ታክሎበት በአሁኑ ወቅት በአጠቃላይ በስድስት ዘርፎች በየአመቱ በየዘርፉ የላቀ ሥራ ለሰው ልጅ አበርክተዋል ለተባሉ ግለሰቦችና ድርጅቶች ሽልማቱ ይበረከታል ።”
ምንጭ ፦ ግሩም የዐለማችን ምርጥ ታሪኮች በግሩም ተበጀ
እኛስ ስንሞት በሕይወት ታሪካችን ላይ እንዲጻፍ እና እንዲነበብልን የምንፈልገው ነገር ምንድን ነው? እሱን እንኑረው ።

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትስስር ይፍጠሩ

325,851FansLike
49,039FollowersFollow
13,194SubscribersSubscribe