ስጦታ ለመውሰድ ሲል ሴት መስሎ ጋብቻ የመሰረተው ጎረምሳ መጨረሻው ዘብጥያ መውረድ ሆኗል

ይህ ሴት መሳይ ጎረምሳ በጋብቻ እንደ ሚስት ለ12 ቀናት ቆይቷል
ሁኔታው ያላማረው ባልም ባደረገው ክትትል በውበቷ ተማርኮ ያገባት ሚስት የ25 ዓመት ጎረምሳ መሆኑን አረጋግጧል
ስጦታ ለመውሰድ ሲል ሴት መስሎ ጋብቻ የመሰረተው ጎረምሳ መጨረሻው ዘብጥያ መውረድ ሆኗል፡፡
በእስያዊቷ ኢንዴኖዢያ የተፈጠረው ክስተት አረ አያድርስ ያስብላል፡፡
ስሙ ያልተጠቀሰው የ26 ዓመቱ ይ ኢንዶኔዢያዊ በፌስቡክ አንድ መልከመልካም ሴት ይተዋወቃል፡፡ ከዚህ ቆንጆ ሴት ጋር በየቀኑ ያወራሉ፣ ይደዋወላሉ፡፡
ይህ መላመድ ወደ ፍቅር አድጎ በአካል ወደ መገናኘት ያመራ ሲሆን ይህም ድግግሞሽ ለረጅም ጊዜ ሲካሄድ ነበር ተብሏል፡፡
በዚች ቆንጆ ፍቅር መውደቁን ያመነው ይህ ሰውም የፍቅር ጥያቄ አቀርቦ ጥያቄውም ተቀባይነት ያገኛል፡፡
በሀገሩ ባህል እና ሀይማኖት መሰረትም ጋብቻ ለመመስረት ይስማማሉ፡፡ ይሁንና ሚስት ለመሆን የተስማችው ይህች ቆንጆ እናቷ በቅርቡ እንደሞተች መላው ቤተሰቧም ሀዘን ላይ በመሆናቸው ሰርጓ ላይ መገኘት እንደማይችሉ ባሏን አሳምናለች፡፡
ባልየውም ቅር እያለው የእሱ ቤተሰቦች በተገኙበት ጋብቻቸው ይፈጸማል፡፡ ልጃቸው ቆንጆ ሚስት በማግባቱ ደስ የተሰኙት የሙሽራው ቤተሰቦችም ከምራታቸው ጋር ለመቀራረብ እና ለመላመድ ቢሞክሩም አልተሳካላቸውም፡፡
ሙሽራው እና ቤተሰቦቹ ባዩት ነገር ቅር መሰኘታቸውን ተከትሎ ጉዳዩን ለማጣራት ይወስናሉ፡፡ እነዚህ ሰዎች ባደረጉት ማጣራትም መልከ መልካሟ ሴት የ25 ዓመት ጎረምሳ መሆኑን ደርሰውበታል ሲል የሀገሪቱ ብዙሃን መገናኛዎች ዘግበዋል፡፡
ጉዳዩን ወደ ፖሊስ የወሰዱት የባል ቤተሰቦችም ሴት መስሎ ያታለላቸው ጎረምሳ ቤተሰቦቹ በህይወት እንዳሉ ጋብቻውን ሴት መስሎ የፈጸመውም ስጦታ ለመቀበል ሲል እንደሆነ ፖሊስ በምርመራው ደርሶበታል፡፡
መዋቢያዎችን እና አልባሳትን ተጠቅሞ ሴት መስሎ ጋብቻ የፈጸመው ጎረምሳም በፖሊስ ተይዞ ለእስር የተዳረገ ሲሆን ባደረገው ማጭበርበር ለተጎጂ ቤተሰቦች የሰርግ ወጪ ካሳ እንዲከፍል ክስ ተመስርቶበታል፡፡
እንዲሁም ለፈጸመው ማጭበርበር ወንጀልም የአራት ዓመት እስር ይጠብቀዋልም ተብሏል፡፡

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትስስር ይፍጠሩ

325,851FansLike
49,039FollowersFollow
13,194SubscribersSubscribe