ቅዱስ ጊዮርጊስ ቢራ እና ስንቅ በጥራት ውድድር የወርቅ ሽልማት መሸነፉን አስታወቀ

የቢጂአይ ኢትዮጵያ ቅዱስ ጊዮርጊስ ቢራ እና ከአልኮል ነጻ የሆነው ስንቅ ምርቶቹ Monde Selection በተባለው ዓለም አቀፍ የምርት ጥራት አወዳዳሪ ድርጅት ተመርጠው የ2022 የወርቅ ሽልማት ማግኘ አስታወቀ፤

የቢጂአይ ኢትዮጵያ ባወጣው ጋዜጣዊ መግለጫ ሁለቱም ብራንዶች ለሽልማት የተመረጡት ቢራና ለስላሳ መጠጦችን ጨምሮ የበርካታ ምርቶችን ጥራት በጥንቃቄ በመገምገም አሸናፊ ብራንዶችን ለክብር በሚመርጠው በMonde Selection ድርጅት ነው ድርጅቱ የመጠጦችን ጥራት የሚገመግው ለዚሁ ዓላማ በተቋቋመው የታዋቂ ባለሙያዎች ሸንጎ አማካይነት ሲሆን ሸንጎው ቴክኒሻኖችን፣ የተመሰከረላቸው የጠመቃ ባለሙያዎችንና የኬሚካል መሐንዲሶችን ያካተተ ነው።
ውድድሩ የምርት ጥራትን ዙሪያ ምላሽ (360) የሚቃኝ ሲሆን በዓለም አቀፍ ደረጃ ለተጠቃሚዎች
በጣም አስፈላጊ የሆኑ እስከ 25 የሚደርሱ መመዘኛዎች ይጠቀማል ከመመዘኛዎቹ መካከል 1) ጣዕም ነክ፤ የመጠጡ ሽታ፣ ሲጠጣና ከተጠጣ በኋላ ያለው ጣዕም፣ አፍ ውስጥ የሚቀር ጣዕምና ስሜት፤
2) የምርቱ ኬሚካላዊ ይዘትና ቅንብር ይገኙበታል፤ እንዲሁም
3) በጠርሙሱ ላይ ለደንበኛ የቀረበው መረጃ
ማጣራት ዋነኞቹ ናቸው፡
ስለሆነም የግምገማ ሂደቱ ከተለመደው ደበኛ ቅምሻ ባሻገር በርካታ መለኪያዎችን በጠቀም የመጠጦቹ ሁለንተናዊ ጥራት የሚመዘንበትን ሂደት ነው፡፡
የኢትዮጵያ የመጀመሪያው ቢራ እንደመሆኑ ቅዱስ ጊዮርጊስ ቢራ የበርካታ ትውልዶች ምርጫ ሆኖ ላለፉት 100 ዓመታት መቆቱን ክቡራን ደንበኞቻችንና መላው የቢጂአይ ቤተሰብ ጠንቅቆ የሚያውቀው ሲሆን የድርጅታችን የጀመሪያው ከአልኮል ነጻ የሆነው ስንቅ ቢራችም በጥቂት ጊዜ ውስጥ ከቁንጮዎቹ መካከል መሰለፉ ፀሐይ የሞቀው እውነት ነው።
ሁለቱ ምርቶቻችን በዓለም አቀፍ መድረክ እውቅና አግኝ+ው የክብር ዘውዶችን መቀዳጀታቸው ለዚህ እውነታ እርግጠኛ ማስረጃ ነው።
በዓለም አቀፍ መድረክ ይህን የመሰለ ክብር ተጎናጽፈን, ለመታየት ከቻልንበት ታሪካዊ ምዕራፍ ላይ አብረን በመድረሳችን መላውን ደንበኞቻችን ፤ አጋሮቻችን እና ለመላው የቢ.ጂ.አይ ቤተሰብ እንኳን ደስ ያላችሁ! ለማለት ይወዳል፡፡
መልካም አዲስ ዓመት!!

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትስስር ይፍጠሩ

325,851FansLike
49,039FollowersFollow
13,194SubscribersSubscribe