ቅድመ ሁኔታዎችን ላሟሉ ለ23 የሃይማኖት መገናኛ ብዙኃን የምዝገባ ሰርተፊኬት ተሰጠ

የሀይማኖት መገናኛ ብዙሃን ተቋማት አብሮነትን የሚያጠናክሩ ስራዎች ላይ ትኩረት ሊያደርጉ ይገባል- የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙሃን ባለስልጣን
 የሀይማኖት መገናኛ ብዙሃን ተቋማት አብሮነትን የሚያጠናክሩ ስራዎች ላይ ትኩረት እንዲያደርጉ የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙሃን ባለስልጣን አሳሰበ።
የሀይማኖት መገናኛ ብዙሃን ለአብሮነት እሴቶች መጠናከር በሚል መሪ ሀሳብ በውይይቱ ላይ የመንግሥት ኮሚኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ከበደ ዴሲሳ ፣የሀይማኖት አባቶች እና መገናኛ ብዙሃን ተወካዮች ተሳትፈዋል፡፡
የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙሃን ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር አቶ መሀመድ እድሪስ እንዳሉት የሀይማኖት መገናኛ ብዙሃን ለትውልድ ግንባታ የአገር ሰላም ላይ ትኩረት ማድረግ አለባቸው።
በአንዳንድ መገናኛ ብዙሃን ዘንድ ልዩነቶችን የሚያጎሉ ስራዎች እየተስተዋሉ መሆኑን ጠቁመው፤ ይህም ለአገር አይበጅም ነው ያሉት።
የሀይማኖት ተቋማት ከፖለቲካ ነጻ ሆነው የራሳቸው እምነት አስተምህሮት ላይ ብቻ ማተኮር እንዳለባቸው አመልክተዋል።
አቶ መሀመድ እንዳሉት የሀይማኖት መገናኛ ብዙሃን ተቋማት ምክር ቤት በማቋቋም ረገድ ሃይማኖት ተቋማት የጀመሩት እንቅስቃሴ የሚበረታታ ነው ።
የኢትዮጵያ ሀይማኖት ተቋማት ጉባኤ ጠቅላይ ጸሐፊ ቀሲስ ታጋይ ታደለ በበኩላቸው የሀይማኖት መገናኛ ብዙሃን የመከባበር መርህን ማክበር አለባቸው ብለዋል ። “እኛ እና እነሱ የሚል አስተሳሰብ መኖር የለበትም” ሲሉም ተናግረዋል።
በመድረኩ የሃይማኖት መገናኛ ብዙኃን የአብሮነት አሴቶችን በማጠናከር እና በሰላም ግንባታ ዙሪያ ሊጫወቱት ስለሚገባው ሚና እንዲሁም የሃይማኖት መገናኛ ብዙኃን የህግ ማዕቀፎች የሚሉ ፅሁፎች ቀርበው ውይይት ተደርጎባቸዋል፡፡
በመጨረሻም ከኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለሥልጣን ለምዝገባ የሚየስፈልጉ ቅድመ ሁኔታዎችን አሟልተው ምዝገባ ላከናወኑ ለ23 የሃይማኖት መገናኛ ብዙኃን የምዝገባ ሰርተፊኬት የመስጠት ስነ-ስርዓት ተከናውኖ ውይይቱ ተጠናቋል።

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትስስር ይፍጠሩ

325,851FansLike
49,039FollowersFollow
13,194SubscribersSubscribe