በህገወጥ መንገድ ተሹመናል ያሉ 17 ግለሰቦች የይቅርታ ደብዳቤ አስገቡ

በህገወጥ መንገድ ሢመተ ኤጲስ ቆጶሳት የተፈጸመላቸውና ተሹመናል ያሉ 17 ግለሰቦች የይቅርታ ደብዳቤ አስገቡ።
ጥር 14 ቀን 2015 ዓ.ም በደቡብ ምዕራብ ሸዋ ሀገረ ስብከት በሶዶ ዳ ወረዳ ከወሊሶ ከተማ ወጣ ብሎ በሚገኘው ሀሮ ባለ ወልድ ቤተ ክርስቲያን ውስጥ የተፈጸመውን እጅግ አሳዛኝ እና ኢ-ሲኖዶሳዊ የሆነ ሕገ ወጥ የቀኖና ቤተ ክርስቲያን ጥሰት የተሳተፉ ግለሰቦች
መጋቢት 19 ቀን 2015 ዓ.ም በጠቅላይ ቤተ ክህነት ከብፁዕ አቡነ አብርሃም እና ከብፁዕ አቡነ ጴጥሮስ ጋር ወይይት በማድረግ የይቅርታ ደብዳቤያቸውን ያስገቡ ሲሆን ደብዳቤውን ብፁዕ አቡነ አብርሃም አንብበው በመቀበል ለቅዱስ ሲኖዶስ እንደሚያቀርቡ ተናግረዋል።
አንድ አባት ደብዳቤ የላኩ ሲሆን ቀሪዎቹ በቅርብ ቀን እንደሚያስገቡ ተገልጿል።
መ/ር ማርቆስ ተበቃ
EOTC TV

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትስስር ይፍጠሩ

325,851FansLike
49,039FollowersFollow
13,194SubscribersSubscribe