በህገ ወጥ መልኩ ሲዘዋወር የነበረ ከ4 ሺህ 600 በላይ ተተኳሽ የክላሽ ጥይት ተያዘ፡፡
በትላንትናው ዕለት ከመቐለ ወደ ባህር ዳር ከተማ ሲጓጓዝ ከነበረ አይሱዙ ኤፍኤስአር መካከለኛ የጭነት ተሽከርካሪ በወልደያ መቆጣጠሪያ ጣቢያ በጉምሩክ ሰራተኞች አማካኝነት በተካሄደ ፍተሻ ብዛቱ 4 ሺህ 615 የሆኑ ተተኳሽ የክላሽ ጥይቶች ተይዘዋል።
ህገ ወጥ የጦር መሳሪያዎቹን በመደበቅ ለማሳለፍ የሞከሩ አሽከርካሪውን ጨምሮ አራት ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር ውለው ተጨማሪ ማጣራት እየተደረገባቸው ይገኛል፡፡
በወልደያ መቆጣጠሪያ ጣቢያ በቅርንጫፍ ጽህፈት ቤቱ አንድ ሳምንት በማይሞላ ጊዜ ውስጥ ብቻ ከ10 ሺህ 600 በላይ ተተኳሽ የክላሽ ጥይቶች በህገ ወጥ መንገድ ሲንቀሳቀሱ መያዛቸውን ከፅህፈት ቤቱ ያገኘኘው መረጃ ያመለክታል።