በደቡብ ኢትዮጽያ ክልል ከ629ሺ ሊትር በላይ ቤንዚንና ከ90ሺ ሊትር በላይ ናፍጣ መያዙን የክልሌ የንድና ገበያ ልማት ቢሮ አስታውቋል፡፡ በተለያዩ የክልሉ ዞኖች በተደረገው ቁጥጥር 629ሺ 910 ሊትር ቤንዚንና 90ሺ665 ሊትር ናፍጣ በቁጥጥር ስር ውሎ ተሸጦ ገንዘቡ ለመንግስት ገቢ መደረጉን ገልጻል፡፡
ክልሉ ህገ ወጥ የነዳጅ ዝውውሩን ለመቆጣጠር ግብረ ኃይል አቋቆሞ እየሰራ እንደሆነም ተናግሯል፡፡ ይህንን በማድረግ በክልሉ ነዳጅ አቅርቦት ላይ አሉታዊ ጫና በማሳደር ችግር እንዲፈጠር በሚያደርጉ አካላት ላይ ህጋዊ እርምጃ መውሰድ እንደተጀመረም ይፋ አድርጓል፡፡//

