በመማሪያ ክፍሎች ውስጥ የሞባይል ስልኮችን መጠቀም በኔዘርላንድ ታገዱ

” ሞባይል ስልኮች የመማር ማስተማሩን ተግባር እንደሚያስተጓጉሉ ከሳይንሳዊ ምርምር ውጤቶች እናውቃለን ” – የኔዘርላንድ ትምህርት ሚኒስትር

የሞባይል ስልኮችን ጨምሮ የመማር ማስተማር ተግባር ሊያስተጓጉሉ ይችላሉ የተባሉ የቴክኖሎጂ ውጤቶች #በኔዘርላንድ ታገዱ።

በመማሪያ ክፍሎች ውስጥ የሞባይል ስልኮችን መጠቀም እንደታገደም የኔዘርላንድ መንግሥት አስታውቋል።

እቅዱ ከትምህርት ቤቶች ጋር በመተባበር ተግባራዊ እንደሚሆን የተገለጸ ሲሆን በአውሮፓውያኑ አዲስ ዓመትም ይጀመራል ተብሏል።

ነገር ግን ልዩ የህክምና ፍላጎት / አካል ጉዳተኛ የሆኑ ተማሪዎች ይህ እግድ እንደማይመለከታቸው ተገልጿል።

በተጨማሪ ዲጂታል ክህሎቶች ላይ በሚያተኩሩ የትምህርት ክፍለ ጊዜውም ላይ እነዚህ የቴክኖሎጂ ውጤቶች እንደሚፈቀዱም ተጠቁሟል።

ይህ እግድ በህጉ ባለመስፈሩ በህጋዊ መንገድ ተፈጻሚ ባይሆንም ወደፊት ግን ሊካተት ይችላል ተብሏል።

የሀገሪቱ የትምህርት ሚኒስትር ምን አሉ ?

ሮበርት ዲጅግራፍ ፦

” የሞባይል ስልኮች ከህይወታችን ጋር ከሞላ ጎደል የተሳሰሩ ቢሆኑም በመማሪያ ክፍሎች ውስጥ ግን መገኘት የለባቸውም።

ተማሪዎች ትኩረታቸውን በደንብ ሰብስበው በጥሩ ሁኔታ እንዲማሩ እድል ሊሰጣቸው ይገባል።

ሞባይል ስልኮች የመማር ማስተማሩን ተግባር እንደሚያስተጓጉሉ ከሳይንሳዊ ምርምር ውጤቶች እናውቃለን።

የተለያዩ ጥናቶች የልጆችን የስክሪን ቆይታ ጊዜ መገደብ ከግንዛቤ እና ትኩረት መሻሻል ጋር እንደሚያያዝ ይጠቁማሉ።

ታብሌቶችና ዘመናዊ ሰዓቶችን ጨምሮ ሌሎች የቴክኖሎጂ ውጤቶች በዚህ እገዳ ውስጥ ተካትተዋል። ”

መንግሥት እነዚህን የቴክኖሎጂ ውጤቶች ሙሉ በሙሉ ማገድን በተመለከተ ትምህርት ቤቶቹ ከመምህራን፣ ወላጆች እና ተማሪዎች ጋር በመምከር ተግባራዊ ሊያደርጉ እንደሚችሉ አስታውቋል።

ይህ እቅድ በሚኒስቴሩ፣ በትምህርት ቤቶች እና ባለ ድርሻ አካላት ተቋማት መካከል የተደረሰ ስምምነት መሆኑ ተገልጿል።

እቅዱ ተግባራዊ ከሆነ በኋላ በአውሮፓውያኑ 2024/2025 የትምህርት ዘመን መጨረሻ ምን ያህል ውጤታማ እንደሆነ ተገምግሞም በህግ ይስፈር የሚለውም ውሳኔ ይደረስበታል ተብሏል።

በተመሳሳይ …

ፊንላንድ የሞባይል ስልኮችን በመማሪያ ክፍሎች ውስጥ የሚያግድ ውሳኔ ባለፈው ሳምንት አስተላልፋለች።

የፊንላንድ መንግሥት በትምህርት ቤቶች ውስጥ ስልኮችን የማገዱን ሁኔታም ወጥ ለማድረግ ህጉን እንደሚያሻሽል አስታውቋል።

ዩናይትድ ኪንግደም እና ፈረንሳይን ጨምሮ ሌሎች አገራትም የመማር ማስተማር ሁኔታውን ለማሻሻል የሞባይል ስልኮችን በመማሪያ ክፍሎች የማገድ ሃሳብ አቅርበዋል።

Via BBC

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትስስር ይፍጠሩ

325,851FansLike
49,039FollowersFollow
13,194SubscribersSubscribe