በማይናማርውስጥ የሳይበር ማጭበርበሪያ ካምፖችን በመምራት የሚታወቀው ቤተሰብ በቻይና የሞት ፍርድ ተላለፈባቸው

በእነዚህ የሳበር ማጭበርበሪያ ካምፖች በርካታ ኢትዮጽያዊያን ለረጅም ጊዚያት በስቃይ ማሰለፋቸው ይታወሳል፡፡

የቻይና ፍርድ ቤት በማይናማር ውስጥ የሳበር ማጭበርበር ተግባር ላይ ተሰማርተው በነበሩ አምስት ዋና የማፍያ ቡድን አባላት ላይ ነው የሞት ፍርድ ያስተላለፈው፡፡

ባይ የተባለው የቤተሰብ አባላት እና አጋሮች የሆኑ 21 ሰዎች በማጭበርበር፡በነፍስ ማጥፋት እና በሌሎች ወንጀሎች የጥፋተኝነት ውሳኔ እንደተላለፈባቸው ቢቢሱ ዘግቧል፡፡

ይሄው የቤተሰብ አጭበርባሪ ቡድን የራሱ የሆነ የታጠቀ ሚሊሻ ያለው ሲሆን 41 ካምፖችም አሉት፡፡ ከ700 የማያንሱ ኢትዮጽያዊያን በእነዚህ የማጭበርበሪያ ካምፖች ተታለው ገብተው ለበርካታ ጊዚያት በአስቸጋሪ ሁኔታ ማሳለፋቸው አይዘነጋም፡፡

ከብዙ የጋራ ጥረት በኋላም ኢትዮጽያዊያኑ ወደ ሀገራቸው እንዲመለሱ መደረጋቸውንም እናስታውሳለን፡፡

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትስስር ይፍጠሩ

325,851FansLike
49,039FollowersFollow
13,194SubscribersSubscribe