በምርጫ ጉዳይ ማህበረሰቡን ለማንቃትና መሰል ስራዎችን ለመስራት ከውጪ የገንዘብ ድጋፍ ማግኘትን የሚከለክለው የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች አዋጅ ለሁለተኛ ጊዜ ሊሻሻል ነው ተባለ

የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶችአዋጅ በስድስት ዓመት ጊዜ ውስጥ ለሁለተኛ ጊዜ ተሻሽሏል ተባለ፡፡

ቀደም ሲል በነበረው ህግ ድርጅቶቹ ከሚያገኙት የገንዘብ ድጋፍ ከ10 በመቶ በላይ ከሃገርና ከውጪ የገንዘብ ምጮች የሚያገኙ ከሆነ በፖለቲካና መብት ላይ እንዳይሰሩ የሚከለክል ነበር፡፡

ይህ የተጠቀሰውና ሌሎችም ለማህበራቱ ማነቆ ሆነው ቆይተዋል የተባሉትን አንቀጾች ተሻሽለው ከ6 ዓመት በፊት ነበር አዋጁ የጸደቀው፡፡

አሁን በአዋጁ ላይ እንደገና እየተደረገ ያለው ማሻሻያ የሲቪል ማህበራት ወደ ቀድሞው ሁኔታ እንዳይመልሳቸው ተሰግቷል፡፡

አዲሱ የህግ ማሻሻያ በምርጫ ጉዳይ ማህበረሰቡን ለማንቃትና መሰል ስራዎችን ለመስራት የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ከውጪ የገንዘብ ድጋፍ ማግኘትን ይከለክላል፡፡//

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትስስር ይፍጠሩ

325,851FansLike
49,039FollowersFollow
13,194SubscribersSubscribe