“በሩን ክፈቱ ሲሉ የነበሩ ግብረ ሰናይ ድርጅቶች የት ሄዱ ብላችሁ ጠይቁ” – አምባሳደር ዲና ሙፍቲ

#Ethiopia : የኢትዮጵያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባዩ አምባሳደር ዲና ፥ ስለሰብዓዊ ቀውስ ሲኮንኑ ለቆዩ ምዕራባዊያንና ግብረ ሰናይ ተቋማት በሩ ክፍት የተደረገላቸው ቢሆንም በቂ ሰብዓዊ ድጋፍ እያደረጉ አይደለም ብለዋል።

አምባሳደር ዲና ሙፍቲ፥ ተርዓዶ የሚሰጡት ተቋማት እንደከዚህ በፊቱ ፍቃድ ሳያስፈልጋቸው ለሰላም ሚኒስቴር አሳውቀው ዝም ብለው እርዳታ ይዘው ወደትግራይ መሄድ ይችላሉ የሚል ውሳኔ ከዚህ በፊት መተላለፉን አስታውሰዋል።

በሩን ክፈቱ ፣ ህዝቡ ተጎድቷል ፣ ተርቧል ፣ እያለ ለሰብዓዊ መብት ሲጮህ የነበረው ኃይል እና ተቋማት በሩ ከተከፈተ በኃላ የሉም ፤ ስለዚህ የት ሄዱ ? ብላችሁ ጠይቁ ሲሉ አምባሳደሩ ተናግረዋል።

እንደነበረው ጥያቄ በእርዳታ ማቅረብ ከፍተኛ መጥለቅለቅ የሚፈጠር የሚመስል ነበር ነገር ግን በሩ ሲከፈት እርዳታ የለም ፤ አንዳንዱ ባዶ ኪሱን መድሃኒትም ፣ ገንዘብም ምንም ሳይዝ ይመጣል ብለዋል።

ምንም እንኳን በትግራይ ለሰብዓዊ እርዳታ ለማቅረብ ለሚሰሩ ድርጅቶች ያልተገደበ ይለፍ የተመቻቸ ቢሆንም አሁንም ድረስ 70% ሰብዓዊ ድጋፍ እየቀረበ ያለው በመንግስት መሆኑን አሳውቀዋል።

Kumneger Media
Kumneger Media
Kumneger Media is a News and Entertainment Website & Channel. Kumneger Media in addition to News and Entertainment it is the hub of Politics, Movies, Drama, Music, Comedy, Documentary and More!

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትስስር ይፍጠሩ

325,851FansLike
49,039FollowersFollow
13,194SubscribersSubscribe